{1} ቅማንትና አካባቢው ላይ ለተፈጠረው የሰላም መደፍረስ ምክንያቶቹ ምንድናቸው ብለው ያምናሉ?
- የቅማንት ህዝብ ጥያቄ በወቅቱና በአግባቡ አለመመለሱ
- የአማራ ክልል መንግስት ህዝቡ ያቀረበውን ጥያቄ የህዝብን ፍላጎት፣ የህግን የበላይነት ተከትሎ በሰላማዊ መንገድ ከመፍታት ይልቅ የሃይል አማራጭ ተጠቅሞ ህዝቡ ያላመነበትንና በጥያቄ ላይ ያለን ጥያቄ እነሱ በሚፈልጉት መንገድ ለማስፈጸም መሞከር፥
- የቅማንት የራስ አስተዳደር ከእነ አካቴው እንዳይቋቋም የሚፈልጉ በክልሉ መንግስትና በመሪ ድርጅቱ ብአዴን ድጋፍ የተደራጁ ሃይሎች (ለምሳሌ አብንና ጎንደርህብረት) በቅንጅት የለየለት አፈናና የዘር ጭፍጨፋ ውስጥ መግባታቸው
- የፌዴራ ልመንግስት ህገ-መንግስቱ በሚያስቀምጠው አግባብ ጣልቃ-ገብቶ ችግሩን በዘላቂነት መፍታት ሲገባው ለፖለቲካ ትርፍ ሲባል ግጭቱን እንደሚፈልገዉ በሚያሳይ መንገድ ጉዳዩን ዳር ሁኖ እየተመለከተ መሆኑን በኦሮሚያ በሶማሊያና ጋምቤላ ክልሎች የተፈጠሩ ችግሮችን ትኩረት ሰጥተዉ ችግር በፈጠሩ አመራሮች ላይ ፈጣን እርምጃ ሲወሰድ ህጻናት ሴትና አረጋዊያን ቤታቸዉ ዉስጥ በእሳት ሲቃጠሉ ሰምቶ እንዳልሰማ ታዛቢ የሆነዉ የፌደራል መንግስት ከክልሉ መንግስት ጎን የተሰለፈ መሆኑን በግልጽ ያሳያል መከላከያ የሚጠበቅበትን ሃላፊነት በአግባቡ እንዳይወጣ ተገቢውን ትእዛዝ ያለመስጠት ችግርና የሚዲያ አፈናውም ከበፊቱ አሁን በባሰ መንገድ መሆኑን እያወቀ ዝምታ መምረጡ
- የቅማንትን ጉዳይ በተመለከተ ከእውነታው ውጭ ለፖለቲካ ፍጆታ ሲባል ያልተገቡ የፖለቲካ ፕሮፓጋንዳዋች ወይም ፍረጃዎች በክልሉ መንግስት ባላስልጣናት በኩል መሰራጨታቸዉ ለምሳሌም በተለያዩ ጊዚያት የቅማንት የማንነት ጥያቄን ከተለያዩ የፖለቲካ ተቃዋሚዋች፥ ከህወሀት ግንቦት ሰብስት፥ ሸአቢያ፥ ጋር በማያያዝ ህብረተሰቡም የዚህ የተዛባ ፕሮፓጋንዳና አመለካከት ተጠቂ እንዲሆን በመሆኑ
- በአገር ውስጥና ከውጭ ያሉ መገናኛ ብዙሃን (እንደ አማራ መገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲእና ኢሳት ያሉት) ከአማራ ክልል መንግስት ጋር በቅንጅትና በተከታታይ የሚያሰራጯቸው የተዛቡ መረጃዎች ግጭቶችን ለመፍጠር እንደ ነዳጅ ሁነው በማቀጣጠል በማገልገላቸው
{2}– ከቅማንት ህዝብ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ዘላቂ ሰላምን ከማስፈን አኳያ ምን መደረግ አለበት ብለዉ ያስባሉ?
- የሚመለከተው አካል ሁሉ የሃይል እርምጃና አማራጭ መንገድን ከልቡ ትቶ በሰላማዊ መንገድ ጉዳዮችን ለመፍታት አቋም መውሰድ ይገባዋል። በድርድርና በውይይት በሰለጠነ መንገድ አንድን የህዝብ ጉዳይ ለመፍታት መለማመድ ያስፈልጋል።
- ከዚህ አኳያ የክልሉ መንግስት ዋናውንና ቀዳሚውን ድርሻ መውሰድ ይጠበቅበታል። በህዝብ ላይ ጦርነት አውጆ ላደረሰው መጠነ-ሰፊ ሰብአዊና ቁሳዊ ጥፋትና ቀውስ ቅማንትንም ሆነ የአማራን ህዝብ በግልጽ ይቅርታ መጠየቅ አለበት።
- የክልሉ መንግስት የቅማንትን ህዝብና ህግን በማክበር የቅማንትን ህዝብ ይሁንታና የህግ እውቅና ያለውን አስተባባሪ ኮሚቴ ከማሳደድ፣ አስሮ ከማሰቃዬት፣ መግደልና ከማፈናቀል ይልቅ በማክበርና በማቅረብ የሰላሙና የዘላቂ መፍትሄው አካል አድርጎ ለመጠቀም መዘጋጀት ይኖርበታል። ኮሚቴውም ድሮም እንደሚያደርገው ለሰላማዊ መፍትሄ ፍለጋ ከመቼውም በላይ ጠንክሮ መስራት ይጠበቅበታል።
- የክልሉ መንግስት የህዝብን ፍላጎት መሰረት አድርጎና ህግን ተከትሎ ዴሞክራሲያዊ ባህርይ ተላብሶ የቀረበውን የራስ አስተዳደር ጥያቄዘላቂና የማያዳግም ምላሽ መስጠት ከቻለ ሰላም ከማምጣት አንጻር አሁንም የመጀመሪያው ጥሩ አማራጭ ይሆናል። ይህ የማይሆን ከሆነ ግን ህገ-መንግስታዊ ስርአቱን ተከትሎ የፌዴራል መንግስቱ የሱማሌን ክልል ችግር ጣልቃ ገብቶ እንደፈታው ሁሉ የቅማንትን ጉዳይም ሊፈታው ይገባል።
- ደግና ሰላም ወዳድ የሆኑ የአማራና ቅማንት ህዝቦችን እየቆሰቆሱ ለማጋጨት ሌት ተቀን የሚሰሩ የተደራጁ ሃይሎችና የመገናኛ ብዙሃን ከዚህ እኩይ ተግባራቸው መቆጠብ ይኖርባቸዋል። መላው የኢትዮጵያ ህዝብም አበክሮ ሊያወግዛቸው ይገባል። በነሱ የተሳሳተ ፕሮፓጋንዳ ህጻናት ሴቶችና እሩጠዉ ማምለጥ ያልቻሉ ቤት ዉስጥ እንዳሉ በሳት ተቃጥለዋል ከሊቢያ በረሀ ከታረዱ ወንድሞቻችን ያልተለየ ድርጊት በህዝባችን ላይ እየተፈጸመ ነዉ።
{3}-የቅማንት ህዝብ በተፈጸመበት ግልጽ የዘር ማጽዳት ጦርነት የአማራ ማስሚዲያ ምንም አይነት ተፈናቃይ የለም በማለት የቅማንትን ህዝብ በጦርነት በርሀብ መሰረታዊ የሰዉ ልጆች አስፈላጊ ነገሮች (ዉሀ ልብስና ምግብ) በመከልከ ግልጽ የዘር ማጥፋት ሲፈጸምበት እርዳታ እንካን እንዳይገባ የተፈናቀለ የለም በማለት ከፍተኛ በደል እየደረሰበት ይገኛል። እስኪ የኢትዮጵያም ሆነ የዓለም ህዝብ ማወቅ ያለበትና ማድረግ ያለበት ካለ የጉዳቱን አስከፊነትና መጠን የሚያስፈልጉ እርዳታዎች ምንድናቸዉ?
- ግድያዉ ከከባድ መሳሪያ እስከ ቤት ዉስጥ በጅምላ ማቃጠልን ያካትታል (ህጻናት ሴትና አረጋዊያን) የሳት ቃጠሎዉ ሰለባ መሆናቸዉን። በሞት ደረጃም በስም በትክክል የታወቁና አድራሻና ስራቸዉ የተረጋገጡ በአንድ መቃብር እስከ 56ሰዎች አስከሬን የተገኘበት ጭፍጨፋ ሲፈጸም በአሀዝ የታወቁት •••••••
በአጠቃላይ መንግስት የቅማንትን ጥያቄ ለመፍታት የሄደበት መንገድ የተሳሳተ መሆኑ ለሰላም መደፍረሱ ዋና ምክንያት ነው። በአለም የምትገኙ ኢትዮጵያዊያንም በሰላማዊ መንገድ ለቀረበ የማንነት ጥያቄ እንደዚህ አይነት ግፍ መፈጸሙን በማዉገዝ ለተፈናቀሉና ለተጎዱ ኢትዮጵያዊያንም ሰዉ በመሆናችሁ ብቻ ማድረግ የሚጠበቅባችሁን እርዳታ በየአላችሁበት ታደርጉ ዘንድ በቅማንት ህዝብ ላይ የክልሉ መንግስት በግልጽ የሚፈጽመዉን አድሎም በማጋለጥ ሀገራችን ወደሰላሟና ልማቷ በጋራ እንድንመልሳትጥሪያችን በቅማንት ህዝብ ስም እናስተላልፋለ።
Recent Comments