ሊያጋሩን የሚፈልጉት ሀሳብ ጥቆማና አስተያየት ካለ ይጻፉልን contact us page የሚለዉን ፔጃችን በመጠቆም። we will respond to you either phone or email your method of contact.
የህግ የበላይነትና አፈና
አንድ ሀገር እድገት ልማትና ሰላም በተረጋገጠ አላት ሊባል የሚችለዉ የህግ የበላይነት በሀገሪቱ ሲረጋገጥ ብቻ ነዉ። ባለስልጣናት ጭምር በህግ የበላይነት ካልተገዙ ባጠፉት ጥፋት ልክ እንደማንኛዉም ህዝብ ተጠያቂ ካልሆኑ አምባገነናዊ ስርአት ይሆናሉ ያለመረጋጋት ምንጭ ደግሞ አምባገነንነት ነዉ።
በዉሸት የሚመራ እንጅ የሚከተል ህዝብ የለም
መሪዎች በተለይም በታዳጊ ሀገራት ህዝብን በመከፋፈልና የተለያዩ የፖለቲካ ፕሮፓጋንዳዎችን በከፋፈሉት መጠን በመቀስቀስ በዉሸት ፕሮፓጋንዳ ዘላቂም ባይሆን የሚከተላቸዉ ያፈራሉ። ተከታዮቻቸዉም ከዘለቄትዊ መፍትሄዎቻቸዉ ይልቅ በጊዜያዊነት ያገኙትን ጥቅም ያስቀድሙና የመንጋ ጉዞው እረጅም ሳይሄድ ህዝቦች በችግሮቻቸዉ አንድ ሆነዉ መንግስታትን ይለዉጣሉ መንግስት የህዝብ ሲሆን መንግስት ደግሞ የህዝብ እቃ ስለሆነ ህዝብን ካልጠቀመና ካላገለገለ ስልጣኑን ለህዝብ መስጠት አለበት።
በሀገረ ኢትዮጵያ ስርአት አልበኝነት ለምን ነገሰ?
ስልጣን ላይ ያለዉ የህዝብን ጥያቄ ትኩረት ሰጥቶ መፍትሄ ከመፈለግ ይልቅ የስልጣን እድሜን ያለስራ ለማራዘም ለግጭት ምክንያት በሚሆኑ እቅዶች ብቻ በማትኮርና ለነዚህ ምክንያቶች የፕሮፓጋንዳ ስራም የመንግስትና የህዝብን ሀብት ንብረት በመጠቀም ግችቶችና ህገወጥ የጦር መሳሪያ ንግድ ባለስልጣናቱ ሲገቡበብት በሌላ መንገድ ደግሞ ወደስልጣን አልጋ በአልጋ መዉጣት የሚፈልገዉ ሀይል የጦር መሳሪያ ንግዱን ከባልስልጣናት ጋር የሽርክና ተጠቃሚ በመሆን በህገወጥ የጦር መሳሪያ ነጋዴዎች ባልስልጣናት ጥበቃና ከለላ ነዉጥ እንዲነሳ በማድረግ ተይዘዉ ወደ ህግ በሚቀርቡ ጊዜም የጥቅም ሸሪኮች ባለስልጣናት እንዲፈቱ በማድረግ ወንጀለኞቹም ስዓት አልበኝነቱን በመጠቀም በህግ የሚከታተላቸዉን የህዝብ አካላት በብቀላ እንዲገደሉ በማድረግ የህግ የበላይነቱ በባለስልጣናት ሊከበርና ሊተገበር ባለመቻሉ ሀገረ ኢትዮፕያ የስርአት አልበኝነት ተጠቂ እየሆነች መጥታለች።
Since 1993
MMN's MaIN GOAL & MESSAGE
የሚዛን ሚዲያ ማህበረሰብ አላማና መልእክት፡
በኢትዮጵያ የሚገኙ የተለያዩ የመንግስትና የግል ሚዲያዎች በአካባቢዉ የሚፈጠረዉን የሰላም አለመረጋጋት በትክክል እየዘገቡ አለሜሆናቸዉን ስንታዘብ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ዉስጥና በዉጭ የሚገኙ የሚዲያ ተቀማት አድሎ እጅግ አሳዛኝ ደረጃ በደረሰበት ወቅት የግል ሚዲያዎች ድምጻቸዉ የታፈኑ ህዝቦችን ድምጽ እንደማሰማት ገንዘብ ለመሰብሰብ ብቻ የሸቀጥ መሳሪያ መሆናቸዉ፥
የመንግስት ሚዲያወችም የባለስልጣናት እስትንፋስ ስለመኖሩ ከመዘገብ ወጥተዉ የህብረተሰቡን ጥያቄ ለመንግስት የመንግስትን ምላሽ ለህዝብ ማቅረብ ሲገባቸዉ በፖለቲካዊ ወገንተኝነት ተጠምደዉ ከህዝብና ከሙያቸዉ ይልቅ የአሁን አለቆቻቸዉን ማስደሰትና ህዝብን ከህዝብ በሚያጋጩ ስራወች ተጠምደዉ የሀገራችን የክልላችን የኢትዮጵያዊያንን ሰላም ሲያናጉ እያየን እየታዘብን ነዉ።
ሚዛን ኢትዮጵያዊያንን ብዙ ምናብ ዉስጥ የሚያስገባ ምልክቱም በህወታችን፥ ጾታ ሳይለይ በሀይማኖታችን፥ በመንግስታት በሰላም በጦርነት በገበሬዉ በከተሜዉ የእለት ከእለት እንቅስቃሴዉ ዉስጥ የሚገኝ የፍትህ፥ የእኩልነትና የህግ የበላይነት የአለም መግባቢያ ምልክት ነዉ።
ስለዚህ ሚዛን ሚዲያ ኔትወርክ እንደስሙ ክብደት ሁሉንም ኢትዮጵያዊያን በእኩልነት ያለአድልዎ በነጻነት በሀሳብ መቀራረብን በመነጋገር መግባባትንና የህግ የበላይነትን መርህ ይዞ የእትዮጵያ ህዝብን እዉነተኛ ድምጽና መረጃ በማቅረብ ድምጻቸዉ ለታፈኑ ድምጽ ይሆናል ብለን እናምናለን። በሀገር ዉስጥም ሆነ በዉጭ የምትገኙ ኢትዮጵያዊያን ሚዛን ሚዲያ ኔትወርክን በመደገፍ ድምፃቸዉ ለታፈኑ ኢትዮጵያዊያን ድምፅ ትሆኑ ዘንድ መልእክታችን ነዉ።