የጠማማዉ ብእር ወለምታ፥ የቅማንት ጥያቄና ቅምዝምዝ

Democracy is not above the Law of Order or constitution!

በዳግማዊ ቴዎድሮስ edited July 06, 2019

በየዓመቱ በሚካሄደው በሰሜንአሜሪካየኢትዮጵያዊያን  የእግርኳስፌስቲቫል ላይለመገኘት በብአዴን/አዴፓ ዋና  ሊቀመንበር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስቴር ደመቀመኮነን የተመራዉ ቡድን ወደ አሜሪካ የአመራው ስፖርቱ ከመጀመሩ ከሣምንት በፊት ነበር:: ማህበራዊ መገናኛዎች እንደዘገቡት የዚህ ጉዞ አላማም 1ኛ) የአመራውን ዳያስፖራ ቀልብ ለማግኘትና  እና 2ኛ) በአማራ ክልል የሚነሱ የዲሞክራሲያዊና የማንነት ጥያቄዎች ምክንያት በሰሜን ጎንደርና በአንዳንድ አካባቢዎች የተፈጠረዉን አለመረጋጋት ወደ ነበረበት ለመመለስ በውጭ አገር ያሉ የአካባቢው ተወላጆችን ለማነጋገር ነበር::  ይህን በ2ኛ ላይ የተገለጸዉንተልዕኮ ለማሳካትም የተቀረፀው አጀንዳ “በጎንደር መስተዳድር ዞኖች በቅማንትና አማራ ማህበረሰብ የተከሰተዉን ደም አፋሳሽ ግጭት ለመፍታት በአዲስ አበባ ከተማ በሚኖሩ የጎንደር ተወላጆች ተነሳሽነት የተቋቋመ የሰላምና እርቅ ኮሚቴ የአጭር ጊዜ የድርጊት መርሀ ግብር” በሚል በ11 ገጾች የተደገፈ የስራ መርሀግብር ይዘዉነዉ:: ሆኖም ግን ልዑካን ቡድናቸዉ ጋር  በማረፊያ ሆቴላቸዉ ዋሽንግተን ዲሲ እንዳሉ በባህርዳርና በአዲስ አበባ ከፍተኛ ባለስልጣናት ላይ በተፈጸመው ሰብአዊነት በጎደለዉ ግድያ ምክንያት ወደ አሜሪካ ያቀኑበትን መርሀ ግብር ሳይጀምሩ ወደ ሀገር ቤት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ተመልሰዋል::   ይሁን እንጅ ከአቶ ደመቀ ጋር ለዚህ ጉዳይ አብረዉ የመጡት የልዑካን ቡድኑ አባላት መርሃ ግብሩን ለአካባቢው ተወላጆች ለማዳረስ ሞክረዋል::  በአትላንታ እንዲሁም በተለያዩ የአሜሪካና የአውሮፓ ከተሞች በተለይ በአማራ ክልል የተፈጠረዉን የሰላም አለመረጋጋት ግምት ዉስጥ ያደረገዉና በአንክሮም በቅማንትና አማራ ህዝቦች መካከል በተፈጠረዉ ግጭት የአዲስ አበባ ነዋሪዎችና የጎንደር ተወላጆች ያዘጋጁት የሰላምና እርቅ አጭር መርሀ ግብር በሚል የቀረበዉ ጽሁፍ በአብዛኛዉ የሰሜን አሜሪካ ግዛቶች የሚኖሩ የጎንደርና የአካባቢዉ ተወላጆች ተቀባብለው አይተውታል መርሀ ግብሩም በቀጥታ ከብአዴን አዴፓ የተዘጋጀና የቀጣይ እቅዱም ምን እንደሚመስል በግልጽ የሚያሳይ መሆኑን ያረጋገጠ ነበር።

የጽሑፋን አላማና ስለጉድለቱም የተለያዩ የአካባቢው ተወላጆች የሀሳብ ክርክር እና ውይይት አድርገዋል፡:  የልዑካን ቡድኑ ያቀረበዉ የመርሀ ግብር በዋናነኛነት ግልጸኝነት የጎደለዉ እና የቅማንት ህዝብ የሚያደረገውን ትግል እንደ ትግል እውቅና የነፈገ እንዲያውም በግልፅ ወደ አንድ ጐን አድላዊነት ያሳየ ኢ-ፍታዊ ፍረጃን የአካተተ እንደሆነ በጉልህ ተለይቶ ተንሸራሽሯል::  በተለይ ደግሞ የትግሉ ባለቤት የሆነው የቅማንት ህዝብና ተወላጆች እየቀረበ ያለው የመከራከሪያ ሀሳብ የህግ የበላይነት ቅድሚያ መከበር ይገባዋል ከሚለዉ ጀምሮ ጎንደር የቅማንትና የአማራ ህዝብ አልተጋጩም፣ በደስታና ሀዘናቸዉ የማይለያዩ ህዝቦችን የተጋጩ በማስመሰል የረከሰ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት በተወሰኑ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች የሚፈጠር ፕሮፓጋንዳ እንጂ በሁለቱ ህዝቦች መካከል ለግድያ የሚያበቃ ችግር ወይም ልዩነት አልነበራቸውም፣ለዚህ ሁሉ ጥፋት ተጠያቂው የመንግስት ባለስልጣናት ናቸው። የቅማንት ትግል እንደ ማንኛውም ብሔር-ብሔረሰቦችና ህዝቦች ትግል ሁሉ የዲሞክራሲና የፍትህ ትግል እንጂ እነሱ  እንደሚያስተጋቡት የ3ኛ ወገን እጅ የሌለበት ትግል መሆኑ ይታወቃል:: ይህን ሐቅ እነሱም ግጥም አድርገው ያውቁታል:: የቅማንት ጥያቄ ህገመንግታዊ ስለሆነ ህገመንግታዊ መልስ ሊሰጠው ይገባል የሚሉት ናቸው:: ሲቀጥልም የተጠየቀው ጥያቄ ጠያቂው ህዝብ፣ተጠያቂው ህገመንግስቱ  እና መንግስት እዛው ከሚያስተዳድሩት መሬት( አገር ) ላይ እያሉ መልስ ፍለጋ ወደ ውጭ አገር መምጣቱ የጉዳዩን ባለቤት የቅማንት ህዝብ ጥያቄ መናቅና ከምንም አለመቁጠራቸዉ አግባብነት የለውም:: መንግስት የሚያስተዳድረውን የቅማንት ህዝብ ወርዶ በነፃነት ያለአድሎአዊነት እና ማሸማቀቅ ሊያወያየው ይገባል:: የሚዲያ ፍትሃዊ ተደራሽንት ሊረጋገጥ ይገባል:: ቅማንት ላይ ሲደረስ ህገ መንግቱ የህግ አግባብ አሰራር ድሃ የሚሆንበት እና ግብር ከፍሎ የሚያድርን ገበሬ በጠራራ ፀሐይ የሚገደልበት እርካሽ ድርጊት ሊቆም ይገባል የሚሉ ሐሳቦች በስፋት ተደምጠዋል:: በሚዲያ ይታፈን እንጅ በየመድረኩ የቅማንት ህዝብ የሚጨሆውም ይህንኑ ነዉ። እዉነታዉ ግን የቅማንት ህዝብ ያቀረበዉ ሰላማዊ የማንነትና የራስ አስተዳደር ጥያቄ በሰላማዊ መንገድ እንዳያልቅ ሆን ተብሎ የክልሉ መንግስት አንድ አንድ ባለስልጣናት ስልጣናቸውን ያለአግባብበ በመጠቀም ልዩ ሐል፣ፋኖ፣ሚኒሻ፣ ፀረ-ሽምቅ እና ሌላም ያለየሌለ ሀይሉን በማሰባሰብና  በበጀትም ድጋፍ በማደራጀት የቅማነት ህዝብ ላይ በማዝመት እና የረከስ እርምጃ በመውሰድ ህዝቡን ማሸማቀቅና በማዳከም የጥያቄውን አቅጣጫ በማስቀዬር ህልሙን ማጨለምና ብሎም ማፈን ነው፡:  በውጭ የሚኖሩና የሚንቀሳቀሱ የአካባቢውተወላጆችንም የሚያግባባበት ሥራ ሊሰራ በተልዕኮ መርሃ ግብር ወደ አሜሪካ የመጣውም ለዚህ ነው::  መመካከሩና መወያዬቱ ምንም ክፋት የለውም::  የቅማንት ህዝብም እባካችሁ እንወያይ አትግደሉን መግደል መልስ አይሆንም እያለ በወከላቸው ኮምቴዎች በኩል ሲለምን ነበር የቆዬው::  ነገር ግን በእኛ ፍላጐት እንጅ የቅማንት ህዝብ በፈለገው መንገድና ህገመንግስቱን  ተከትሎ እራሱንመምራት አይችልም በማለት ሕገመንግስታዊ መብትን በጠመንጃ አፈሙዝ እና ማንኛውንም ስለታማ መቆራረጫዎች በመጠቀም ከቅማንት ህዝብ ላይ ያራገፈው:: በአሁኑ ሰዓት አንፃራዊ ሰላም ያለ ቢመስልም ሙሉ በሙሉ አልቆመም:: የእርዳታ አሰጣጡና መልሦ የማቋቋም ስራዉም ቢሆን በአድሎና በኢፍታዊነት የዘቀጠ: የተጨመላለቀና የተበላሸ እንደሆነ ይስተዋላል ይታያል ይሰማል::  ቅማንት ይህ ሁሉ ችግር የደረሰበት በራሱ ቀዬ ላይ በቤቱ ውስጥ ነው:: ሞተ እንጅ አልገደለም:: በመግደል ተፃያፊ ህዝብ ነው:: የክልሉ መንግስት ወደቀልቡ ተመልሶ ጥያቄውን መልሦ ጠረጴዛ ላይ አስቀምጦ በውይይት እና በህጋዊ መንገድ ይመለስ ዘንድ መንገድ እንዲያመቻቸ፣ በግልፅ ህዝቡን ወረዶ እንደያወያይ፣ አጉል በሬ ወለደ አይነት የጥላቻ የሚዲያ ዘመቻ የሚያደርጉ ሚዲያዎችንና ጋዜጠኞችን ተጠያቂ እንዲያደርግ:: የክልሉ መንግስት ከአድሎአዊነት የሥራ ባህሪው ተላቆ ቅድሚያ ሊሰሩ የሚገባቸውን ሥራዎች ትኩረት ስጥቶ ሊሰራቸው ቢችል ወደ ሰላም መሄድ ይቻላል::  ህዝብ የወከለው ኮሚቴን ማሣደድ እና ያለስሙ ስም በመስጠት ያለምንም ጥፋትም ይቅርታ ይጠይቁ በማለት ማሳደዱ እንዲቆምና ህጋዊሥራውን እንዲጀምር፣ ህይወት ያጠፋ የሰጠፉ  ንብረት ያወደሙ፣ ያቀጠሉ፣ የዘረፉና ያዘረፉ ግለሰቦች እና ባለስልጣናት ለህግ እንዲቀርቡ እንዲያደርግ፣ የቅማንት ባለሐብቶች ተመልሰው ወደ ስራቸው የሚመለሱበትን መንገድ በአስቸኳይ እንዲዘጋጅ፣ ከብቶችን በእሳት ያቃጠሉና ወንድሞቻችን በስለት የቆራረጡ አረመኔዎች ለፍርድ እንዲቀርቡ ይደረግ:: የተፈናቀሉ ገበሬዎችም ሆኑ የመንግስት ሰራተኞችና ነጋዴዎች ወደ የሥራና ቦታቸው የመኖሪያ ቀያቸቸው (ቤታቸው)  ተመልሰዉ እንዲቋቋሙና አስፈላጊውን ድጋፍ እንደደረግላቸው እና በዘላቂነትም የህልውና ጥበቃ እንዲደረግላቸው:: እንዲሁም በአድሎ ተፈረዶባቸው እና ሳይፈረድባቸው በየእስርቤቱ ያሉቅማንቶች ትክክለኛ ፍርድ እንዲያገኙ ስንል በትህትና እንጠይቃለን:: ይህ ከተደረገ ነገሮች በተፈጥሮ ሂደታቸው ጭምር ወደ ተሻለ መግባባት ያመራሉ::  ነገር ግን በቅድሚያ እነዚህ ሳይሰሩ እየበደሉ እርቅና ውይይት እንዴት ሊኖር ይችላል?  ስለ መልዕክተኛው የምክትል  ጠቅላይ  ሚኒስትር ደመቀ መኮነን ቡድን ስንመለከትም መወያዬት ክፋት ባይኖረውም በቀረበዉ ንድፈ ሀሳብ ከመርሀ ግብሩ ጀርባ ያሉጥያቄዎች ግልፅ መሆን ግን አለባቸው:: ግልጸኝነት ከሌላቸዉ የመርሀ ግብሩ ጽሁፍ ዉስጥ ጥቂቶቹ፦

1ኛ) በአዲስ አበባ የሚኖሩ የጎንደር ተወላጆች የሰላምና እርቅ ኮሚቴ የሚባለዉ ማነዉ? የኮሚቴዉ ስም ዝርዝር ከቀረበዉ ጽሁፍ ጋር በግልጽ ለምን አብሮ አልቀረበም?

2ኛ) ሁላችንም እንደምናዉቀዉ ከለዉጡ በሁላ በዶ/ር አብይ አቅራቢነት የብሄራዊ እርቅና ሰላም ኮሚሽን (Ethiopian National peace and Reconciliation Commission) በካርዲናል ብርሀነ እየሱስሰ ብሳቢነትና በወይዘሮ የትነበርሽ ንጉሴ ምክትል ሰብሳቢነት እንዲሁም በቀድሞዉ ጠቅላይ ሚኒስተር ሐይለማሪያም ደሳለኝ በአቅም ግንባታ ስልጠና እና በፋይናስም የሌሎች ሀገሮችን ድጋፍ ለማግኘት  መመረጣቸዉና ኮሚሽኑም በተወካዮች ም/ቤት መቐቐሙን እናዉቃለን። በመርሀ ግብሩ ጽሁፍ አቅራቢ አንደበት እንደተረዳነዉና በጽሁፉ ርእስም እንደምናነበዉ ማንኛዉንም የመንግስትም ሆነ የፖለቲካ ድርጅቶችን የማይወክል ከሆነ በመንግስት ደረጃ በተወካዮች ም/ቤት ጸድቆ የተቐቐመ ተቐም እያለ በተቃራኒዉ በጎንደር ተወላጆች ስም ሌላ የሽምግልና ቡድን ማቐቐሙ ለምን አስፈለገ? ጠቅላይ ሚ/ር ዶክተር አብይ ለነዚህ የድንበር የሰላምና እርቅኮሚሽን ተመራጮች ገለልተኝነት ሲያሳስቡ የሽማግሌ የመጀመሪያዉ መመዘኛ ገለልተኛ መሆኑ ነዉ አሉና ሽማግሌ ሀይማኖት፥ ዘር፥ ሀገርና ፓርቲ የለዉም።  ይህ ደግሞ በመቶ አመት አንዴ የሚያጋጥመን እድል በመሆኑ በአግባቡ እንጠቀምበት ነበር ያሉት። የቀረበዉን ጽሁፍ በአወንታዊነቱ እንቀበለዉ እንዀዋን ብንል መንግስት ካቐቐመዉ ተቐም ጋር እንደሚቃረንና ሀላፊነትና ተጠሪነቱ ግልጸኝነት የጎደለዉ ድብብቆሽ አካሄድ በሽምግልና የማይፈቱ ነገር ግን በህግ አግባብ እልባት ሊያገኙ የሚገባቸዉ ጉዳዮች ቢያጋጥሙ ሀላፊነትና ተጠያቂነት የሌለዉ አካሄድ ለተጨማሪ  የፖለቲካ ሴራ የተጠመደ ወጥመድ መሆኑን በመገንዘብ ከጅምሩ ጥፋተኛ ብሎ  ወስኖ በሽምግልና ስም የቀረበ መርሀ ግብር በመሆኑ፥

3ኛ) እስከ መቸ በዉሸት ጥላ ተደብቀን በክልላችን ዉስጥ ያሉ መጥፎ አመለካከቶችን የመደበቂያ ዋሻ ሆነን “የጎንደርን ሰላም ለማደፍረስ አጀንዳ አድርገዉ የሚንቀሳቀሱ ሶስተኛ ወገን”  እያልን እራሳችን እየዋሸንና እያታለልን የኢትዮጵያ ህዝብ ደግሞ እዉነታዉን ከወሬ አልፎ በክልሉ የሚፈጸሙ አድሎአዊ አሰራሮችን ዉጤት  በአይኑ እየተመለከተ ባለበት ሰአት የህዝቡን ሰላም እየነሳ ያለዉን አካል በጀብዶ ሽልማት ከማበረታታት ይልቅ ለመምከር፥ ለመገሰጽና ለማስተካከል የሚያስችል ግልጽ መርሀ ግብር በጽሁፉ ላይ አልታየም። ጎንደር የቅማንትና የአማራ ህዝቦች በአንድ ድምጽ የሚጠይቁት የቅማንትን ጥያቄ በአስቸዃይ መልስ ሰጥታችሁ እባካችሁ ወደ ልማታችን እንግባ፥ በተለይ መሪወች በሴራ ፖለቲካ አጀንዳ እየፈጠራችሁ ሰላማዊ ኑሮአችን አትበጥብጡት የሚል ነዉ። በዚህ ጽሁፍ የሽምግልና የእርቅ ኮሚቴ በሚል የቀረበዉ ጽሁፍ ግን ስራዉን ሳይጀምር የጥፋት ሀይል፥ አጀንዳ ተቀባይ እያለ ጥፋተኟዉ ይቅርታ እንዳይጠይቅ ገለልተኛ አለመሆኑን በሚያሳይ መንገድ በግልጽ የቅማንት ኮሚቴዎች ጥፋተኛ ስለሆኑ ይቅርታ ይጠይቁ ሲል ሳይጀምር ዉሳኔዉን አስቀምጣል። ለመሆኑ የጥፋት ሀይል፥ አጀንዳ ተቀባይ ተብሎ የተገለጸዉ ሀይል ማነዉ?

4ኛ) ብቸኛዉ የሰላም መንገድ የህግ የበላይነት ነዉ። የችግሩ መነሻ የቅማንት ህዝብ ያቀረበዉ የመብት ጥያቄ ሲሆን የክልሉ መንግስት ከተለያዩ ጉዳቶች በሁላ ቢሆንም የሰጣቸዉን ምላሾች እያደነቅን የተⶓተተዉ የፍትህ አሰጣጥ በመሀሉ የሴራ ፖለቲካ ቡድኖችን እየወለዱ በሚፈጥሩት ህዉከት ሴረኞችን ለመደበቅም ጉዳዩ የማይመለከተዉን የአማራና የቅማንት ህዝቦች ግጭት በማለት በበላይነት በሚቆጣጠሩዋቸዉ መንግስታዊና የግል ሚዲያወች ማራገባቸዉ እየታወቀና ተቀባይነትም እንደሌለዉ እየታወቀ የህግ የበላይነትም ጊዜ የማይሰጠዉ big picture  ሆኖ እያለ በቀረበዉ የጽሁፍ መርሀ ግብር የተሰጠዉ ቦታ ባለመኖሩ  ህግና እዉነታን መሰረት አድርጎ በሁለቱ የቅማንትና የአማራ ህዝቦች ከአዲስ አበባ እና ባህርዳር በባለስልጣናት በሚመረጡ ሽማግሌዎች ሳይሆን ከቦታዉ በህዝቡ በተመረጡ የሰላምና እርቅ ገለልተኛ ኮሚቴዎች ከተሰራ ከህግ በላይ ባይሆንም ግብአቱ ቀላል አይሆንም ብለን እናምናለን። ይህ ያልታወቀዉ ኮሚቴ ግን ከጅምሩ ከመርሀ ግብሩ ርእስእ ንደምናነበዉ  “በቅማንትና አማራ ማህበረሰብ የተከሰተዉን ደም አፋሳሽ ግጭት ለመፍታት” ከሚለዉ ርእስ ጀምሮ ገለልተኛነት የጎደለዉ ጥያቄውን እንደ ጥያቄ እውቅና የነፈገ አሁንም “የሦስተኛ እጅአለበት” በማለት እንደሌሎች ጥያቄው ያልተመቻቸው አቀንቃኞች የአባባል አባዜ ያልተላቀቀ ነው።

5ኛ) የጎንደር የቅማንትና የአማራ ህዝብ ችግሮቹን በባህላዊ መንገድ በሽምግልና መፍታ አዲሱ አይደለም። የህዝባችን ችግር ስለእዉነትም የሚጨንቀን ከሆነ ፊደል ቆጠርን የምንል መስራት የሚጠበቅብን ብዙ ስራ እያለብን፥ ያስተማረን ህዝባችን የህግ የበላይነት እንዲከበርለት፥ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በእኩልነት ያለ አድሎ፥ አፈናና ጫና ቢሮክራሲያዊ አሰራሮች የሌለባት አገር እንድትኖረን በጋራ እንታገል፥ የዲሞክራሲያዊ ተቐማት ሚና እንዲኖራቸዉ ስለ ህግ የበላይነት እና የዴሞክራሲያዊ መብቶቻችን ልዩነት ለተቀላቀለበት ትዉልዳችን እናስተምር፥ በምድረ አሜሪካም ነዋሪ የሆን ትዉልደ ኢትዮጵያዊያንም ብዙ ጠቃሚ ትምህርቶችን ለሀገራችን ህዝቦች ማድረስ እየቻልን እንደማእበል ጎርፍ በመንጋ እየተነዳን ወደ ሴራ ፖለቲካ እየተጠለፍን (እየተጎተትን) በአንጃ የሚከፋፈሉ መሪዎቻችን እያበረታታን ህዝባችን ወደ ባሰ ችግር አናስገባው።

6ኛ) የቅማንት ህዝብ የሚፈልገዉ (outcome) ምንም ይሁን ምን በህግና በህግ አስፈጻሚ አካላት ፊት በማንነቱ ከማንም የማይበልጥ ከማንም ደግሞ በፍጹም የማያንስ መሆኑን ለማረጋገጥ በእኩልነት በአብሮነት በኢትዮጵያ ህግ እኩል እንዲታይ ለመብቱ የሚታገል እንጅ የማንም ተላላኪ ሆኖ የተለየ ጥቅም ለማግኘት አጉል መስዋእትነትን የሚከፍል ህዝብ አይደለም። የአማራ እህት ወንድሙ ህመም፥ መከፋት የቅማንት ህዝብም መከፋትና ህመም መሆኑን ያለመጠራጠር ያዉቃል። ነገር ግን የቅማንት ህዝብ ሲከፋ፥ ግልጽ ጦርነት ሲታወጅበት በደስታና በፍቅር ተሳስቦ የሚኖሩ እህት ወንድም ህዝቦችን “የቅማንትና የአማራ ህዝብ ግጭት” በማስመሰል በቃላት ሊገለጹ የሚዘገንኑ ድርጊቶች በህጻናት ሴቶችና አረጋዊያን ላይ ሲፈጸም ዝም ብሎ የተመለከተ በእህት ወንድሙ ሞት የተደሰተ የአማራና የቅማንት ምሁር ከህሊናው ጋር ሁሌም ተጣልቶ እንደሚኖር ብንገነዘብም ለዚያ የዋህ ህዝብ ዉለታዉ ግን ዝምታ አልነበረም። በመሆኑም ማንም ይሁን ማን ወንጀል የፈጸመ በህግ እንዳይጠየቅ የሚቃወም አንድም የቅማንት ህዝብ የለም። በህጋዊ መንገድ የቅማንት ህዝብ የመረጣቸዉን የህዝብ ኮሚቴዎችን ወንጀለኛ ተላላኪ፥  እጅእንቆርጣለን ብሎ ከመዛት እና ፈርጆ ጦርነት ከማወጅ በፊት እዉነታዉን በማጣራት ሶስተኛ ወገን ብለዉ ከሚያሙት ወገን ጋር ግንኙነት አላቸዉ ተብሎ የሚጠረጠሩ ቢኖሩ እንካን በማስረጃተ ረጋግጦ በህግ እንዲዳኙ በማድረግ የህግ የበላይነት እንዲከበር ማድረግ ይቻል ነበር። ከዚህ ዉጭ እዉነተኛ የጎንደርና የኢትዮጵያን ሰላም ለማምጣት በተለይ ደግሞ በቅማንትና የአማራ ክልል መንግስት (እነሱ እንደሚሉት የአማራና የቅማንት ግጭት) የቅማንት ህዝብ ተመራጭ ኮሚቴዎችን ያላካተተ የሰላም ድርድርየ ህልም ጉዞ መሆኑን በመገንዘብ፥ በህዝብ የተመረጡ ኮሚቴዎችን የመፍትሄ አካሉ በማድረግ የሚታለመዉ የሰላምና የእርቅ ብቸኛዉ መንገድ መሆኑን በመገንዘብ የቀረበዉ መርሀ ግብር ፍኖተ ካርታ ተስተካክሎ በግልጽ ሊያወያይ በሚችልበት መንገድ የአማራ ክልል መንግስት በረጋና በጽሞና ቢመለከተዉ መፍትሄዉም በራሱ በክልሉ መንግስት እጅ በመሆኑ የተሻለ ሀሳብም ሊገኝበት ይችላል ብለን እናምናለን።

7ኛ) ሌላው በቀረበዉ የመርሀ ግብር ጽሁፍ የግልጸኝነት ችግር ከታየበት አንዱ ስለሚዲያ የቀረበዉ ነዉ። ለጎንደርና አካባቢዋ የሰላምና ግጭት ትልቁን የጸባ ጫሪነት ሚና የተጫወተዉ የፌደራልና የአማራ ክልል መገናኛ ብዙሀን የፈጸሙት የአድሎና የአፈና ዘገባ ነዉ። ተጨባጭ ማስረጃ በሌለዉ የበሬ ወለደ ድራማ (አኬልዳማ) በመስራት በተለይ የአማራ ማስሚዲያ የተጫወተዉ አድሎና አፈና የጋዜጠኝነትና የሚዲያ ስነምግባርን የጣሰ ከመሆኑ በላይ ለችግሩ  መባባስ ትልቁ ቆስቐሽ እንደነበር እየታወቀ ከቀረበዉ የመርሀ ግብር ጽሁፍ እንደምንረዳዉ ግን የቅማንትን ህዝብ ግፍ፥ ጭቆና፥ አድሎና አፈና ያጋለጡ እዉነተኛ ሚዲያዋችን ለመወንጀል የተሞከረ ከመሆኑም በላይ የነበረዉ የሚዲያ አፈናና አድሎ በነበረበት እንዲቀጥል የሚደግፍና የሚያበረታታ ጽሁፍ (ገጽ8) ገለልተኛነቱ ግልጽ አለመሆኑን ባረጋገጠዉ የሽምግልና ኮሚቴ መርሀግብር መቅረቡ ይህ ጽሁፍና አዘጋጁ ግልጸኝነት የጎደለዉ አድሎአዊነቱንም አስቀድሞ ያረጋገጠ በመሆኑ

8ኛ) በመጨረሻም ሊያስጨንቀን የሚገባው ትልቁ ቁልፍ ነገር በክልሉም ይሁን በሀገሪቱ የሚነሱትን ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ጥያቄዎች በዉይይት ምክንያታዊና አሳማኝ ማስረጃ ጋር መፍታት እየተቻለ በሀይልና በጦርነት ለማፈን መሞከር ጉዳቱ ለሁሉም በመሂኑ፥  በምንም አይነት መመዘኛም ተቀባይነት የሌለዉ በመሆኑንና በተለይ ደግሞ እህትና ወንድም የቅማንትና አማራ ህዝቦችን እንደተጋጩ በማስመሰል ሌሎችን ለማደናገር የሚሰራጨዉ የተዛባ  ቅስቀሳና የሴራ ፖለቲካ ፕሮፓጋንዳ ሴረኞችን ደብቆ የህግ የበላይነት እንዳይረጋገጥ ከማድረጉ በተጨማሪ፥ በደስታና በችግር ተጋብቶ አብሮ ለኖረዉ የቅማንት ህዝብ ያልቆመ ለእኛ እንዴት ታማኝይሆንልናል  በሚል የተሳሳተ ፕሮፓጋንዳ በሌሎች ብሄር ብሄረሰቦች ለአማራና አማራ ሳይሆኑ አማርኛ ተናጋሪዎች የሚደርሰዉን ፈተና ወደ ነበረበት ለመመለስ የምንሰራው ከባድ ስራ ሆኖ እያለ አሁንም ግልጸኝነት ለጎደለዉ የሴራ ፖለቲካ ባንዳ ሆነን የቅማንት ህዝብ ያቀረበዉን ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ጥያቄ አዳዲስ አጀንዳዎችን በየጊዜዉ በመፍጠር ላለመመለስ ከእዉነት በሸሸን ቁጥር በመላዉ ኢትዮጵያ የሚኖር ህዝባችን ለአደጋ ከማጋለጥ አልፈን ከአሁን በፊት የተፈጸሙትን ስህተቶች ለመድገም የምናፋጥናቸዉን እሩጫዎች ቆም ብለን ማስተዋል የሚገባን ሰዓት ነዉ ብለን እናምናለን። የወርቅ ጃኬት ለብሶ በቅማንትና አማራ ህዝብ ስም የረከሰ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ግጭቶችን እንደ ግብአት የሚጠቀሙ ባለስልጣናትንና ሌሎች ሀይሎችን እንዲያስተካክሉ፥ የህግ የበላይነትን እንዲያከብሩ ምክር የሚሹበት ወቅት ላይ ነን። እዉቅና ያለዉ የሰላምና እርቅ ኮሚቴ ስራዉን በተገቢዉ ቢፈጽም እንኰዋን የህግ የበላይነት ካልተረጋገጠ ዋስትና የሌለዉና ለሚያጋጥሙ ሌሎች ችግሮችም ጠያቂና ተጠያቂ የሌለዉ አጀማመር በደንብ ተመርምሮ ባለስልጣናትም ሆኑ ዴሞክራሲ ከህግ በታች መሆናቸዉን በመገንዘብ ስለጎንደር ሰላም ካስጨነቀን በግልጽ በመነጋገር የችግሩ መነሻ የቅማንት የማንነትና የራስ አስተዳደር ጥያቄና የመንግስት ምላሽ ወየም የተጟተተ ፍትህ እንደተነፈገ ይቆጠራል እንዲሉ፥ የተⶓተተው የመንግስት ፍትህ መሆኑ ተሰምሮበት ወደ ትክክለኛዉ ስላምም ይሁን ወደ መፍትሄዉ ለመሄድ የህግ የበላይነትን በማስቀደም ነጻና ግልጽ ዉይይት በማድረግ የጎንደርን ችግር ልጆቹ መፍታት የምንችል መሆኑን ታምኖበት በግልም ይሁን በመንግስት የዚህ መርሀ ግብር አዘጋጂ በግልጽ እነዚህን ጉዳዮች ያካተተ መሆን አለበት እንላለን።

 

Leave a Reply