By Dagmawi Tewodros September 5,2019

ክፍል አንድ፡

የቅማንት ህዝብ የማንነትና የራስ አስተዳደር ይከበርልኝ ህገመንግስታዊ የመብትጥያቄ  የመነሳቱ ምክንያት በ1999 ዓ/ም የቤቶችና ህዝብ ቆጠራ ላይ የአማራ ክልል መንግስት ቅማንት የሚለዉን የብሄር ስም ሌሎች በማለት ተክቶ ይዞ ቀረበ በዚህ ወቅት የቅማንት ብሔረሰብ እኛ ቅማንንት ነን የብሔራችን ስያሜ በለሌበት ምንም መረጃ አንሰጥም በማለት አቤቱታዉ ከገበሬ  ጀምሮ የተማሩ የቅማንት የመብት ተከራካሪዎች ድረስ ከፍተኛ ተቃዉሞ አስነሳ። በዚሁ አመተ ምህረት ሐያ አምስት  አባላት ያለዉ የቅማንት የማንነትና የራስ አስተዳደር ይከበርልኝ ኮሚቴ ህዝቡ መረጠ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ለአማራ ክልል በቢሔሩ ላይ እየደረሰ ያለዉን ተጽኖ እና መጠሪያዉን መሰረዝ የህዝቡን ባህል ቋንቋ ለማዳከም ሆን ተብሎ እንደ አጼዎች ቋንቋዉን ሲናገር ሀጢያት ገባ ብለዉ ጨደር ሲጠምቁት እደነበረዉ በዚህ ወቅትም ያነን ለመድገም የተደረገ ሴራ ነዉ በማለት የተሰረዘዉ ማንነቱና የራስ አስተዳደር ይከበርልኝ ጥያቄዉን   ለአማራ ክልል መንግስት አቀረበ። ከዚህ ጊዜ ጀምሮ የቅማንት የመንግስት ሰራተኞች ላይ ከፍተኛ የማሸማቀቅ ዘመቻ ተጀመረ። የመሰረተ ልማት ወደ ቅማንት ህዝብወደሚኖርባቸዉ ወረዳና ቀበሌዎች እዳይሄዱ ተደረገ።  በህዝቡ ላይ ከፍተኛ ጫና ማድረግ ማሰር፥ ከተቻለ  መግደል  ማፈናቀል የክልሉ መንግስት በተደራጀ መልኩ ቀጠለበት።  ጫናዉን ተቕቁሞ የቅማንት ህዝብ ጥያቄዉን አጠናክሮ ቀጠለ የቅማንት ኮሚቴና ህዝቡ ባደረገዉ ቆራጥ ትግል የአማራ ክልል ምክርቤት በተደጋጋሚ ተሰብስቦ የሚገርሙ ዉሳኔዎችን አስተላለፈ።ከዉሳኔዎች በትንሹም፦

ዉሳኔ 1:

የቅማንንት ህዝብ አለ የለም ብሎ መናገር ባይቻልም አሁን ግን በአማራ ተዉጧል (ዶሚኔት) ሆኗል እናም የቅማንት ብሄር የሚባል ጠፍቷል በማለት ወሰነ። በዚህ ዉሳኔ ወቅት የቅማንንትን ህዝብ በመናቅ  ምክር ቤቱ የብሄርን አይደለም የግለሰብ መብት በሚከበርበት ወቅት ህዝቡን  ዘለፉ ከተለያዩ ስሞች ጋር በማላተምም ስም ማጥፍት ዘመቻዉን አጠናክረዉ ቀጠሉ ስልጣን ፈላጊዎች አሎቸዉ፥ ከስራ አፈናቀሎቸዉ፥ አሸማቀቛቸዉ፥ በሰበብ አስባቡ ማሰር ጀመሩ።  በዚህ ያልተንበረከከዉ የቅማንት ኮሚቴና ህዝቡ በይበልጥ ቁርኝቱን ቀጠለ በዚህ የተበሳጨዉ የክልሉና የዞን አመራር በመደራጀት በህዝቡ ላይ ዘመቻ ተጀመረ።  የመተማና አካባቢዋ ባለሀብት የቅማንንት ገበሬዎችን መሬታቸዉን በመቀማት ማሰርና  ለመግደል ሙከራ አደረጉ።  የህዝቡ ጥያቄ መንግስት ለማስተዳደር አልመች በማለቱ በየመድረኩ የቅማንት ጥያቄ ዋና መወያያ አጀንዳ ሆነ ብአዴንም ለመሸንገል ሌላ እቅድ አወጣ።

ዉሳኔ 2፡፦

የአማራ ክልል  ምክር ቤት ዉሳኔ ቅማንት በአማራ ክልል በሰሜን ጎንደር በአማራዉ ዉስጥ አልፎ አልፎ አለ። ባደረግነዉ ጥናት ሆኖም እራሱን ግን ማስተዳደር አይችልም በማለት ወሰነ። በዚህ ዉሳኔ ያልተስማማዉ የቅማንት ህዝብ ምክርቤቱ ያሳየዉን ትንሽ ሙከራ አድንቆ በተሰጠዉ ዉሳኔ ግን አሁንም ጥያቄየ አልተመለሰም በማለት ለሚመለከተዉ የመንግስት ተቆማት በይግባኝ  አቤቱታ ማቅረቡን ቀጠለ። በህዝቡ ጽናት የተደናገጠዉ የአማራ ክልል ባለስልጣናት በሌላ እቅድ ተመለሱ የቅማንት ባለሀብቶችና ኮሚቴዉን ለማሰር አቀደ የብአዴን አዲሱ እቅድም የቅማንት ህዝቦችን የማንነትና የራስ አስተዳደር ይከበርልኝ ጥያቄ ይደግፍሉ ሚባሉ ባለሀብቶችን የመጀመሪያዉ የጥቃት ሰለባ ለማድረግ እቅድ ማዘጋጀት ጀመረ በዚህ እቅዱ በደንብ ተሳክቶለታል። ለቅማንት ህዝብ አይደለም ለሱዳን ሰራዊት ማርከሻ የነበረዉን የግል ባለሀብት ጠገነ ወላዉ የቅዱ መጀመሪያ አደረገ ጠገነ ወለላዉ /የበርበሬዉጭስ/ በመባል የሚጠራዉ ማነዉ? ጠገነ ወላዉ የቅማንት ኢንበስተር ሲሆን ከመተማ እስከ ሱዳን አስጨንቆ የአገሪቱን ደንበር ሳይቀር ያስከበረ ባለሀብት ነበር።   እሳቱን አለዚያ ዉሀዉን ምረጥ የቅማንትን ጥያቄ አለመመለስ አደጋ እንዳለዉ አስረግጦ ይነግራቸዉ ነበር። እባብ ያየ በልጥ ይሮጣል እንዲሉ የሰሜን  ጎንደር አመራር ከክልል ባለስልጣናት ጋር በመምከር ይህ ግለሰብ ካለ የቅማንትን ጥያቄ ማኮላሸት ዘበት ነዉ በማለት መከሩ። ሰዉየዉ የብአዴን ተላላኪዎች አይደለም ጎረቤት ሱዳን ወታደር ሳይቀር የሚርበተበቱለት ጀግና ኩሩ ቅማንት ነበር። ዘመቻዉን በሱ ጀመሩ የብአዲን አመራር ከወረዳ እስከ ክልል የግንቦት ሰባት አባል ሆነዉ ሳለ እሱን በግንቦት ሰባት አበልነት በመፈረጂ በድብቅ ያፈላልጉት ጀመር።   በርሀ ከርሻ ከርሞ ድካሙን ለማስታገስ ከተማ ሲገባ ከቅጥረኞች ጋር በመተባበር ምርጡን ባለሐብት አስገደሉት።

በሰአቱ አብሮት የነበረ የአማራ ተወላጂ ጓደኛዉም አብሮ ተገደለ።  ከሱ ጋር በሰአቱ የነበሩ የቅማንት ልጆች በጂምላ ታፍነዉ ወደ እስር ቤት ገቡ በሰአቱ ምክንያቱ ሳይታወቅ በተመሳሳይ ሰአት የጸጥታ ሀይሎችም ተገደሉ።  ያለምንም ማጣራት በትዉልድ ቅማንት የሆነ ሁሉ ወደ እስር ተወስዶ ታሰረ። በዚህ የተበሳጨዉ የቅማንት ህዝብ በንዴት ጀግና ልጆን ባይኑ ሳያለቅስ በልቡ እያለቀሰ በልክና በንዴት ቀበረ  ይህ በአካባቢዉና  በህዝብ የታወቀ በመሆኑ እንጂ ብዙዎቹ ቅማንት ተወላጂ በመሆናቸዉ የተገደሉ የትየ ለሌ ናቸዉ። ከዛ በሆላም የቅማንት ኮሚቴዎች በክልሉ ልዩ ሀይል በአንቡላንስ ከየቤታቸዉ ካፈኑ ሁሉም የቅማንት ኮሚቴ ባለበት በሌሊት ተያዘ አይከል መተማ ጎንደር ወህኒ ቤቶች እስር ቤት እያለ የቅማንትን ህዝብ በገንዘብና በጉልበት ለማዳከም  ከአይከል ወደ ዳባት እስር ቤት በቁጥር ሀያ ሁለት የሚሆኑ የቅማንት አስተባባሪ ኮሚቴ ተወሰዱ። ከዳባት እስር ቤት ወደ ፍርድ ቤት ሲሄዱ ቅማንት ከምን  የሚያዉቀው ጫማ ነዉ በማለት  በእግራችሁ ሂዱ ተባሉ ያን ያህል መንገድ ለህዝብ ሲሉ ደሙ በሾህ በስንጥር በድንጋይ ተወጉ እነሱም  ቅንጅት በመባል አዲስ ታድጋ ተሰጣቸዉ።  ለወራቶችም ታሰሩ በእስር ወቅታቸዉ የቅማንት ህዝብ ኮሚቴ ከዚህ በሆላ ህዝብ ነዉ በማለት አወጀ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የወጣቱ ከፍተኛ እንቅስቃሴ ተፋፋመ ትምህርት ቤቶች ቢሮዎች በአድማ ተዘጉ ከፍተኛ ሰልፎች በጎንደር በአይከል በመተማ ተከናወኑ ይህን የህዝብ መአበል ብአዴን ለማስቆም  አድማበታኝ ከተለያየ ቦታ አሰባሰበ የቅማንት ህዝብም አልበገር ባይነቱን አሳየ ተማሪዎች ወጣቶችን መደብደብና ማሰር ጀመረ በጣም የሚያሳዝነዉ አንድ አባት የ85 አመት ሽማግሌ ልጆቸ ማንነታችሁን ከማጣት መሞት ይሻላል ብለዉ ተናገሩ  በሶስተኛዉ ቀን የክልሉ ልዩ ሀይል ሽማግሌዉን ደበደቡ። የህዝቡ መአበል ከዳር እስከዳር ተቀጣጠለ  የቅማንትን ትግል ከብአዴን አልፎ ፌድራል ድረስ ደረሰ በዚህም የተነሳ ከበላይ በመታዘዛቸዉ የታሰሩት ተፈቱ አሁንም ሌላ ዉሳኔ የአማራ ክልል ምክር ቤት እንደገና  አስተላለፈ።

ዉሳኔ 3

የቅማንት ህዝብ ማንነቱ ተከብሮ  በ42  ቀበሌ እራሱን ያስተዳድራል  በማለት የተከበረዉ ምክር ቤት አድሏዊ ዉሳኔን በተሳሳተ የብአዴን ካድሬዎች መረጃ ድጋሜ  አስተላለፈ። የቅማንት ህዝብም ህገመንግስት ባለበት አገር ዲሞክራሲ በሰፈነበት አገራችን ላይ ምክር ቤቱ የሄደበትን እርምጃ እያደነቅን በብአዴን አባገነንካድሬዎች የህዝቦችን መብት በመጫን ሰጪና ነሽ ሆኖ (ትዮጵያዊነታችን የሚሰጠንና የሚነፍገን አካል እራሱን የፈጠረ ቡድን ለምክር ቤቱ በሚሰጠዉ የተሳሳተ መረጃ ስህተት ተደገመ) ዉሳኔዉም የተሳሳተ ነዉ በማለት የቅማንት ህዝብ አስተባባሪ ኮሚቴ ለፌድራል ቅሬታ አቀረበ። ይህን ህዝብ በምንም መንገድ ሊሸዉዱት አልቻሉም ሌላ ከፍተኛ እቅድ ወይም አኬልዳማ አቀዱለት።  ብአዴን በዚህ ወቅት ታሪክ የማይረሳዉ ጠባሳ በቅማንት ህዝብ ላይ ፈጸመ። በዚህ ወቅት አራስ እናቶች ከራሳቸዉ ያለዉ ግራምጣ ሳይደርቅ ከነመንታ ልጆች  በአሰቃቂ ሁኔታ በካራና በጥይት በአማራ ክልል ልዩ ሐይል  ታረዱ ተገደሉ።

ዉሳኔ4፦ 

ትልቅ  የዘር ማጥፋት የተፈጸመዉ በዚህ ወቅት ነበር የአማራ ክልል ምክር ቤት የቅማንትን ህዝብ በ42 ቀበሌ ይኖራል ብሎ ሲጸድቅ በምክር ቤቱ ይህን የማይቀበል አካል የተከፈለዉ መሰዋትነት በመክፈል እናስፈጽማለን በማለት በህዝብ ምክር ቤት አቶ ገዱ አንዳርጋቸዉ በአሁኑ ሰአት የለዉጥ ሀይል በሚል በዶ/ር አብይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዘመን የዉጭ ጉዳይ ሚኒስተር የተሸለሙት የክልሉ ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ ገዱ አንዳርጋቸዉ በቅማንት ህዝብ ላይ ዛቱ።  ይህን የሰማ የቅማንት ህዝብ ከንዴት ይልቅ በማስተዋል ቅሬታዉን ወደ ፌድራል አቀረበ። የክልልና የዞን አመራሮችም የቅማንትን ጥያቄ ለማፈን በሰፊዉ መወያየት ቀጠሉ  የቅማንት ህዝብም በተለያየ ቦታ ሰልፍ በማድረግ ተቃዉሞዉን ገለጸ። በዚህም የተነሳ በአይከል ከተማ ሰኔ7/2007 እ. ኢ. አ  የተቃዉሞ ሰልፍ ለማድረግ ሰኔ 6 /2007 እለተ ቅዳሜ የክልሉ ልዩ ሀይል ከቀኑ ሰባት ሰአት ባደባባይ አምስት ህጻናትን አንድ የእስልምና ተከታይ ሽማግን  ሶስት ወጣቶችን  በጥይት ጨፍጭፎ ገደለ በርካቶች ቆሰሉ በዚህን ሰአት የገቢያ ቀን ስለነበር ገበሬዉ ንብረቱን ተዘረፈ ወጣቶችን የክልሉ ልዩ ሀይል በየቤቱ እየገባ ደበደበ፥ በጂምላ አሰረ፥ ሴቶች ተደፈሩ፥  ለተከታታይ አንድ ሳምንት ወደ ከተማዋ ከተለያየ ቦታ የሰፈሩ የክልሉ ልዩ ሀይሎች ተሰባስችቡ በዛን ወቅት ከአንድ ሺ በላይ የታጠቀ አካል የቅማንትን ህዝብ ማሳደድ ጀመረ የቅማንት ኮሚቴዎችን እንዲገድል በክልሉ ትዛዝ የተሰጠዉ ይህ ቡድን  ኮሚቴዉን ለመግደልም ሆነ ለማፈን ፍለጋዉን ቀጠለ  የባለሀብቶች ሀብት፥ ሆቴል በመሳሪያ ተደበደበ። የአካባቢዉህዝብ ግን ወደ ገጠር በመዉጣት መደራጀቱን ቀጠለ።   የቅማንት ኮሚቴ ከስንት እንግልት በሆላ ወደ አንድ አካባቢ ተሰባሰበ። ጋባጋላገር ከምትባል የቅማንት ቀበሌ ከህዝቡ ጋር በአደረጃጀት እዉቅና እንዲኖረዉ በሰፊዉ ሰሩ። ህዝቡም በመታጠቅ ሸፈተ በየጎሬዉ በየጣሻዉ የራሱን አደረጃጀት ፈጠረ የክልሉ ልዩ ሀይል ከተማዉ ላይ ያለዉን ኮሚቴና ተቆርቆሪ ግለሰቦችን ግማሹን አሰረ ግማሹን አሳደደ ከዛ በሆላ በነጻነት አርባ ሁለት  ቀበሌ ለማቛቋም የክልሉ አመራር ምቹ ሁኔታ ተፈጠረ በማለት በየቀበሌዉ የቀበሌ ምክር ቤት ጠራ። ሆኖም ግን ህዝብ ያላመነበትን ተግባር አንፈጽምም በማለት  አንድም ገበሬ ሳይመጣ ቀረ። በዚህ ያላረፉት የክልል አመራር ገበሬዉን ለማስገደድ ሞከሩ ለዛ የሚሆን ጠንካራ የታጠቀ ሀይል ያስፈልጋል።  ከልዩ ሀይሉ ጋር በቅንጂት የሚሰራ ታጣቂ ከጫንድባ ነጋዴ ባህርና ሌሎች ቀበሌዎች ሚኒሻ በማሰባሰብ ማደራጀት ጀመሩ።  የቅማንትን ገበሬ ለማስገደድ ጉዙ ወደ ጮንጮቅ ቀበሌተደረገአካባቢዉ ሲደርሱ ግን እንደጠበቁት አላገኙትም። ኬላ ተጥሎ ጠበቃቸዉ በሀይል ለመግባት ሞከሩ ቀድሞ ዝግጂት አርጎ የነበረዉ የቅማንት ገበሬ ማንም ወደ ቀበሌያችን መግባት ከሞከረ ዉርድ ከራሴ አለ የሄደዉ ጽንፈኛ ቡድን በገበሬዉ ላይ ተኩስ ከፈተ የአካባቢዉ  ገበሬ የአካባቢዉ ገበሬ እራሱን ለመከላከል በየአቅጣጫዉ የመልስ ተኩሱን ጀመረ የቅማንት አርሶአደር የሚሞትበት ምክንያት አለዉ። ማንነቱ፥ ቅማንትነቱ። ከገበሬዉ የዘመተዉ ግሬሳ ግን የተወሰኑ ባለስልጣናትን ከማስደሰት ዉጭ አላማ አልነበረዉም። መዉጫ ቀዳዳ ጠፋ። ከአንድ ሰአት የተኩስ ልዉዉጥ በሆላ  የቅማንት ገበሬ ከመከላከል ወደ ጥቃት እራሱንና ሌላዉን የቅማንት እህት ወንድሙን ንብስ ለማትረፍ ከመከላከል ወደ ማጥቃት ገብቶ አራት  ልዩ ሀይሎች ሲቆስሉ ከቦታዉም መሽሽት ጀመሩ። ከቤቱ ጦርነት የታወጀበት ገበሬ የአፋኞችን ተለለኪ ሀይል ወደ መጣበት መለሳቸዉ። በዛ መሀል አንድ የቅማንት ጀግና ወጣት ተገደለ ሲሳይ ድንቁ ይባላል። ከልጁ ጀግንነት የተነሳ ብዙ ተጻፈለት በየመድረኩ ስለቅማንት ተገጠመ ተቀሰቀሰ  በዚህ ያልተሳካለት የክልሉ አመራር በጎንደር በኩል ሮቢት በሚባል ቦታ ልዩ ሀይል ማስፈር አጠናክሮ ጀመረ፥ በዚህ ተግባሩ ምን እንዳሰበ የገባዉ የቅማንት ህዝብ   በሀገር ሽማግሌ በተለያዩ ሰዎች ካምፕ ያደረጓቸዉን ት/ቤቶችና የልማት ተቋማት እዲለቁ ቢጠይቅም ሀይል ከመጨመር በቀር ከአካባቢዉ እደማይወጣ አሳወቀ።  የህዝብ ት/ቤቶችና የልማት ተቋማት የአማራ ክልል ልዩ ሀይል ካምፕ ሆኑ  መማር ማስተማር ስርአቱን አስቆሙት። የጦርነት ነጋሪት መሆኑ የገባዉ ገበሬም ከልዩ ሀይሉ በላይ ዝግጂት ማድረግ ጀመረ። ሽርጉዱ በሁለቱም በኩል ቀጠለ የተለያዩ የቅማንት አካባቢዎችም ህብረተሰቡ የሚመጣባቸዉን  ሁሉ ለመመከት ወይም ለመከላከል ተዘጋጀ።

ዉሳኔ 5፦

ማዉራ! ማዉራ!  ማዉራ! ምን ተፈጠረ ይህን ስታነቡ በህልም ወይም ለወሬ ማድመቂያ የተጻፈ መነባንብ ሊመስላችሁ ይችል። በተለይ ከአማራ ክልል ዉጭ የምትኖሩ ብሔረሰቦች፥ ነገር ግን በ21ኛዉ  ክፍለ ዘመን ያለምንም መረጃ በአድሎና አፈና ዓለም እንዳይሰማ እንዳያዉቅ ክልሉ ያቀደዉ ደባ በወቅቱ የተሳካለት ቢሆንም የቅማንት ህዝብ ተጋድሎ እና የኢትዮጵያ መንግስት ተወካዮች ምክር ቤትም ያረጋገጠዉ እዉነተኛ ታሪክ ነዉ።  ታሪክ ግን እንዲህ ያወጣዋል።  ከዚህ ቀጥሎ የምታነቡት፥ የምትመለከቱት ፎቶና ቪዲዮ እዉነተኛ የቅማንት ህዝብ ታሪክ  ነዉ። አዎ በሁለቱም በኩል ዝግጂቱ ቀጠለ ነገር ግን የቅማንት የሐገር ሽማግሌዎች ከመዳማት ከመገዳደል መሸማገል ኢትዮጲያዊ ባሀላችን ነዉ ተረጋጉ በማለት  ወደ ልዩ ሀይሎች በኩል ለሽምግልና አቀኑ ልጆቻችን እኛ ብንሞትም  አባቶቻችሁን ወንድሞቻችሁን ነዉ የምትገሉት እኛም ብንገድ ልልጆቻችንን ነዉ ከዚህ ያላችሁ የገዛ ልጆቻችን ናችሁ እባካችሁ ደም አይፍሰስ አሉ። የአማራ ክልል መሪዎች የሐገር ሽማግሌዎችን ከምንም ሊቆጥሩ አልቻሉም። የንቀት ሁኔታቸዉን በትዝብት በማየት ሽማግሌዎች  ተመለሱ። እንግዲህ ልጆቻችን በሐገር የመጣን አሳፍረን እንጂ አፍረን አናዉቅም። ስለዚህ ከናተ ጋር እንሰለፋለን በማለት ደርግን አንቀጥቅጦ ድባቅ በመቱበት፥ ድርቡሽን ድራሹን ያጠፉበትን እረጂም ምንሽር ከተቀመጠበት አነሱ። በልዩ ሀይሉ በኩል በየቦታዉ  መትረይስ ተጠመደ። መተንኮስ የማያዉቀዉ የቅማንት ገበሬም በዝምታ ቦታዉን ይዞ ጠበቀ። ከዛኛዉ መንደር  የመክፈቻ ጥሪ ተላለፈ የምላሽ ተኩስ ከገበሬዉ ተሰጠ፥ አገር፥ ህግ፥ መንግስት አለበ ማለት ለአራት  ሰአታት ያህል የቅማንት ገበሬ በመከላከል ቀጠለ። ገበሬዉ ከመዳማት ህግ በአስቸዃይ ገብቶ ያስቆማል ብሎ በማሰብ ታገሰ። ነገር  መንግስት ደግሞ ይበለዉ በሚመስል መንገድ ዝም አለ መታገሱን፥ አልሞ መምታት እዳቃተዉ ያሰበዉ ልዩ ሀይል ወደ ገበሬዉ ቀረበ። የአንዱን ቀምቸ ለአንዱ እሰጣለሁ የሚለዉና በሙስና የተጨማለቀዉ የአማራ ክልል አንዳንድ ባለስልጣናት ተላላኪ ባንዳዎች የሆነዉ የክልሉ ልዩ ሐይል ተጠጋ አሁን ቁርጥ ሆነ  የቅማንት ገበሬም ከመከላከል ወደ ማጥቃት ተዘዋወረ። አዎ እንዃን ገበሬዉ የቅማንት መሬት ለልጆቹ አብሮ ይዋጋል። በሁለቱም በኩል ሚወድቀዉ በዛ ሆኖም መትረይስ ተዃሾች ወደፊት ሊያስጠጎቸዉ አልቻሉም። ከቅማንት መትረይስ ባይኖርም በረዥም ምንሽር፥ በጓንዴ፥ በአብራራዉ በርቀት መትረይስ ተኳሾች ላይ በሽማግሌዎች የጣሊያንና የድርቡሽን ዉጊያ ስልት እንዲጠቀሙና  እዲወገዱ ትዛዝ ተላለፈ። ሲፈልግ ሸምጋይ፥ ሲፈልግ ገበሬ አባሮ አራሽ፥ ካሰኘዉ ወታደር መሆንን የሚያዉቅበት ባለረዥም ምንሽር በተመሳሳይ አልሞተዃሽ ባለመትረይሶችን  አነጣጥሮ መታ።  ከዛም  ከመትረይሱ ማን ይጠጋ በረዥም ምንሽር አይኑን ከዛዉ እደተከለ ተቀበለ። በዚህ እፎይ ያለዉ የቅማንት ገበሬ ወጣት በዛና በዚህ በዱላና በድንጋይ ሳይቀር የወንድሙን አስከሬን እየዘለለ ሲተናነቅ ዉሎ ከምሽቱ አንድ ሰአት ተኩሱ እረብ አለ። በጣም የሚገርመዉ በአንድ መንደር ድንጋይ ተወረወረ ብሎ ቱልቱላ የሚነፋዉ ኢሳት እንኳን ዝም ጭጭ አሉ። አንድም ሰዉ አንድም ድህረ ገጽ በዝምታ እያዩ አብሶም  በፈረንሳይ ተወላጆች ላይ የቦንብ ፍንዳታና  ጉዳት ያገሬ ህዝብ የፌስ ቡክ ገጹን ሳይቀር በፈረንሳይ ባንዴራ ሲቀይር በቅማንት ህዝብ ላይ እዳልሰማ እዳላየ የሚዲያ አድሎና አፈናዉ እንደቀጠለ ከወደ ጎንደር ልዩ ሀይል አቅም ለመፍጠር መጫን ጀመረ። ወደሮቢት ማዉራ በምሽት የሚመጣዉ  በቅማንት መሬት ነዉ። ጦርነቱን የሰማ የአካባቢዉ ገበሬ መንገዱን ቆረጦ ጎድቦ መጠበቅ ጀመረ አገር አማን ብሎ ልዩ ሀይል ከጓደኞቹ ለመድረስ ሲሮጥ የቅማንት ወጣት ከመንገድ የደፈጣ ጥቃት ጣለ። መዉጣትም መግባትም ጭንቅ ሆነ አይነጋ የለ በዚህ መልኩ ነጋ። በጧት የቅማንት ገበሬ የጎደለ ካለ እያሟላ አካባቢዉን መቆጣጠር ጀመረ። እስካሁን ምንም ችግር አላጋጠመም ምንክንያቱም ማዉራ የወዳጁ ማር ለጠላት ግን ፈተና የሆነ መዉጫ መግቢዉ ግራ ሚያጋባ መሬት አቀማመጥ ያለዉ ሆኖ ድንጋዩ እንኳን ሰዉ ዝሆን ይከልላል። በሁለተኛዉ ቀን የጦርነት ዉሎ ከባድ ነበር በሁለቱም በኩል የወኔና የልክ፥ ያልደፈርም ባይነት ዉጊያ ተጀመረ። ምንም ጠላት ሆነዉ የቅማንትን ህዝብ ሊገሉ መጥተዉ ጦርነቱ ቢቀጥልም እነሱም ኢትዮጲያዊ አልደፈርም ወኔ ነበረባቸዉና በተለያየ አቅጣጫ ጦርነቱ ቀጠለ። ቅማንቱ ከቦታዉ ወጥቶ ጥቃቱን ቀጠለ። በማስለቀቅ ላይ እንዳለ አንድ ቁልፍ ሰዉ ወደቀ ብዙዎች የልዩ ሀይል አባላትም ተገደሉ። ወጣቱ ስሜታዊ ነበር በቁም በግላጭ እየሮጠ ወደ ጠላት ተጠጋ።   በዚህ ሰአት የጓደኛዉ መቁሰል አቅሉን ያሳተዉ  የቅማንት ወጣት እየበረረ ያገኘዉን እየጣለ በስሜት ከጎደኞቹ እርቆ ከልዩ  ሀይሎች መሀል ገባ ሚጥለዉን ጥሉ ወደቀ በዚህ ልጂ መሞት ብዙዎቹ እጃቸዉ ሳይቀር በደም ተዘፈዘፈ ጀግና ሚለዉ ብቻ አይገልጸዉም ወጣትነቱ ለሐገሩ ለወገኑ ብዙ ሚሰራዉ በለጋነቱ ሲቀጭ ሽማግሎች አዛዉንቶችም በልጆቻቸዉ ሞት ይበልጥ ተቀጣጠለ ካንተ በፊት እኛ ነበር የምንወድቅ በማለት መሳሪያዉ በልዩ ሀይል እዳትሄድ ከቦታዉ ለማስለቀቅ የተወሰኑት ተሰዉተዉ የጀግናዉን ክላሽና የሟችን አስከሬን በጃቸዉ አደረጉ። በዚህ ልጂ መላዉ የቅማንት ተወላጅ በንዴት ጨሰ በዚህ ሁኔታ ቀኑ ወደ ምሸት ተቀየረ በጣም የሚያሳዝነዉ ከቀናት ዉጊያ በሗላ ኢሳት የተለመደዉን የዉሸት ዘገባዉን   የአማራ ገበሬ ከግንቦት ሰባት ጋር በመሆን የህዋትን ሰራዊት በማጥቃት ላይ ነዉ ብሎ በሬ ወለደ የተለመደዉን የአድሎና የዉሸት ዘገባዉን አስተላለፈ።  እስቡት የቅማንት ህዝብ  ምን  ያህል ግፍ እደገጠመዉ። የአማራ ገበሬና ግንቦት ሰባት ብዙዎችን እደገደለና መሳሪያ እንደማረከ ተናገረ። የጀግንነት ታሪኮች ላም ባልዋለበት ኩቤት ለቀማ በዚህ መልክ ማግኘት ተፈለገ።  ምሽቱ ላይ ጦርነቱ እርገብ አለ በዛን ሰአት መሳሪያ ያልያዙ ገበሬዎች የቆሰሉትን ወደ ሗላ  በመዉሰድ የሞቱትን በመገነዝ ተጠመዱ ከዛኛዉ ወገን ግን ድምጽ የለም  ሀይላቸዉን መጨመር ሆነ ስንቅ ማቅረብ አልቻሉም። ጎንደርና ዙሪያዋ በገበሬዉ ታጥራ ተጠብቃለች።  ምሽቱም ወደ ለሊት ተቀየረ ልዩ ሀይልም በግርግር ወደ ማዉራ ለመግባት ሐይሉን በማጠናከር ሲሞክር ንጋቱ አካባቢ እራቅ ካለ ቦታ የተኩስ ልዉዉጥ ተሰማ፥  ሁሉም ትኩረት አደረገ በግምት ከ30  ደቂቃ ተኩስ በሆላ ቆመ። መረጃ ምንድንነዉ? ተባለ ከማዉራ ግንባር ወደ እናተ ሊመጡ ብለዉ ነዉ ሽፍቶች አልተሳካላቸዉም ተባሉ። ከዛኛዉ ጫፍ በርቱ በማለት አካባቢዉን በማጠናከር  በሶስተኛዉ ቀን  ጀግናዉ አለበል አንጋሽ በጀግንነት በፉከራ ተቀበረ።

በዚሁ ቀን ጥቅምት 29/2008  የፌድራል ፖሊስ ባንዴራ ይዞ ገባ እናም ባንዲራ ማለት አገር ነዉ፥ በመሀል ሚሸመግል ሲገባ ሽማግሌን ማይንቀዉ የቅማንት ህዝብ ተኩሱን አቆመ። ከልዩ ሀይል ሁለት  ከቅማንት ህዝብ ሁለት ተወካይ በመገኘት ከሁለቱም በኩል የሞቱትን እዲያነሱ ባሉበት እንዲጠብቁና ምንም አይነት ትንኮሳ እንደማያደርጉ ተግባቡ። በዚህ ስምምነት  መሰረት የልዩ ሀይሉ በነበረበት የሰዉ እጥረት ማንሳት ያልቻለዉን በየቦታዉ ማንሳት ጀመረ ከሚገመተዉ በላይ ብዙዎቹ መዳን ሚችሉ ደም ፈሶባቸዉ ለህክምና ሳይደርሱ የሞቱ ሁሉ ገጠሙት።  ከተወሰኑት በስተቀር አብዛኞቹ ከጎናቸዉ መሳሪያ አለመገኘቱ ይበልጥ አበሳጫቸዉ፥ የሚያዉቋቸዉ ጓደኞቻቸዉ በህወት የሉም።የዚህ ጦርነት ዘግናኙን ክፍል ባጭሩ በተኩስ አቁሙ መካከል የደረሰበትን ዉድቀት በቁጥር ለማካካስ ልዩ ሀይሉ ወደ መኖሪያ ቤቶች ተሾልኮ በመግባት ወላድ እናት ላይ ያልደረቀ ግራምጣ ያሰረች አራስን  እስከመንታ ልጆቿ በካራ አረዱ፥ ህጻናትን እየተጫወቱ በገጀራ ከተከቷቸዉ ነብሰጡር ሆዷን ቀደዱ በሰዉ ተደግፈዉ የሚወጡ የሚገቡ አረጋዊያን ሽማግሌዎች በስለት ገደሉ ከጀግኖች ተራ ወጥዉ የተራ ሽፍታ ስራ የወደቀባቸዉን የሰዉ ሀይል የቁጥር ማሞያ በሚዘገንን ሁኔታ ፈጸሙ የክልልሉ ልዩ ሀይል ፈጸመ። በዚህ ተግባራቸዉ የቅማንት ህዝብ ከሰዉነት ወዳ አዉሬነት በሊቪያ በረሀ እህት ወንድሞቻችን ካረዱት አይሲሶች የከፋ ድርጊት በእህት ወንድሞቻቸዉ ላይ ሲፈጽሙ ይህ ድርጊታቸዉ በዚህ እንደማይቆምም ተገነዘበ።  በየትኛዉም አለም በሚደረጉ ጦርነቶች  ያለቀ የጦር ሀይል ቢያልቅ ለሴቶችና ህጻናት ከለላ ይሰጣል እንጂ ሚገል የተማረከ እንኳን በእንክብካቤ ነዉ የሚያዝ። በምንወዳት ሀገራችን ኢትዮጵያ አማራ ክልል ግን ይህን ኢሰባዊ ድርጊት አረጉት። በአካባቢዉ የሰፈሩ የፌድራል አካላት አፈሩ። እንደ ህዝቡም ስቅስቅ ብለዉ አለቀሱ ከአንድ ቀን ቆይታ በሗላ የአማራ ክልል ልዩ ሐይል ከአካባቢዉ እንዲወጣ ተደረገ። የመንግስት ባለስልጣናት መጥተዉ የአዞ እንባቸዉን አነቡ ፋይዳ የለለዉ እየየ። የቅማንትልጂ ግን ለመጡት አካላት የክልሉን መንግስ አድሎ አሻጥርና የህግ የበላይነት እንዳይከበር የሚፈጽመዉን ግፍ ፊት ለፊት እንዲህ አቀረቡ፦ የቅማንት ልጂ ከዚህ በሗላ ያስተዉላል ይመረምራል ከዛም ይመታል።

ህግ ከለላ ሊሆነን አልቻለም በማለት ለመጡት አካላት አቀረበ።  ነገር ግን ክልሉ በዚህ የሚያርፍ አይደለም የቅማንት ህዝብን ከምድረ ገጽ ካላጠፋ ማረፊያ ያጣዉ የአማራ ክልል ልዩ ሀይልና መንግስት ከሳሽም፥ መስካሪም፥ አሳሪና ፈራጅ ከፈለገም ገዳይ የክልልሉን ሰላምና መረጋጋት የሚጠሉ አንዳንድ ከፍተኛ ባለስልጣናት በዉጭ ዶላር አይኑን ሸፍኖ እነሱ እንደፈለጉ በሚያጦዟት ፖለቲካ  የአማራ ክልል መንግስት አደለም ለቅማንት ሕዝብ ለኢትዮጵያ መንግስትና ሕገ መንግስት ላይም ሸፍቷል። ።

ዉሳኔ6፦

የክልሉ የመጨረሻ አማራጭ ስም በማጥፋት ህዝብን በመቀስቀስ ወደ ሚቀጥለዉ የጥፋት አኬልዳማ ጀመረ።  የቅማንትን ጥያቄ ላለመመለስ ከበረከት ስሞኦንና ከትግራይ ጋር በማገናኘት በስዉር በህዝብ ላይ አመፅ ማስነሳት በፋኖ ስምም በአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስተር ዶ/ር አብይ መንግስት መጀመሪያ በይቅርታ የተፈቱ ሰዎችንና ምልስ ወታደሮችን በማስታጠቅ በቅማንት ህዝብ ላይ ሌላ ጦርነት ለመክፈት ተዘጋጁ።  መነሻዉ ደግሞ በ2009 የትግሬ ተወላጆችን  ቤትና ንብረት ዘረፋ የቅማንት ህዝብ አለመሳተፉ ነዉ። የቅማንት ህዝብ በመሰረቱ ስርቆትና የሰዉ ንብረት መመኘት በነዉርነት የሚጠየፈዉ ተግባር ነዉ ቅማንት አርሶ መብላት እንጂ በዘሩ ስርቆት በመሀበረሰቡ የተወገዘ ነዉ። በ2009 እ. ኢ. አ. በመተማና  በሽንፋ ቀበሌ ከ300 በላይ የሚደርሱ የትግራይ ተወላጆች  ላይ ዘረፋና ጥቃት  ሊደርስባቸዉ ሲል እነኝህ ትዉልደ ትግራይ ኢትዮጵያዊ ዜጎች ከመተማና ሽንፋ በመሸሽት ህይወታቸዉን ለማትረፍ የቅማንት ህዝብ ወደ ሚኖርባቸዉ ጉባይ ጀጀቢት ተጠጉ። ሆኖም ከክልል እስከ ቀበሌ በተለይ ደግሞ በምዕራብ ኢትዮጵያ በፋኖ የሚመራዉ ቡድንና የክልሉ ልዩ ሀይል የሰዉን ልጅ እንደ ሰዉ ሳይቆጥር ለመግደልና ለማገላታት ዘመቻ ጀመረ። ጀግናዉ የቅማንት ህዝብ ግን እኛን ብሎ የመጣ እኛን ይመስላል እነሱን ምትገሉት እኛን መግደል ከቻላችሁ ብቻ ነዉ በማለት በተለመደዉ የሽምግልና ደንብ ቢጠይቅም በቅማንት ህዝብ ላይ የሚያሳዩት ንቀት ከልክ አለፈ። የቅማንት ህዝብም እራሱን ለመከላከል  ዝግጂት አደረገ። በዚህ የተነሳ ከዚህ በፊት የቅማንትን አቅም ያዉቅ የነበረዉ የክልሉ ልዩ ሀይል ተመለሰ። በዚህ ወቅት እንግዳ ማለት እግዛብሄር ነዉ እንግዳ መቀበል ባህሉ የሆነዉ የቅማንት ህዝብም ለሶስት ቀናት በሬዉን አርዶ፥ ወተት አቅርቦ፥ አልጋዉን ለቆ አስተናገደ። በመጨረሻም መከላከያ ከቦታዉ ድረስ በመሄድ የዝቡን ሰብአዊነት አድንቆ ወደ ትዉልድ  ሀገራቸዉ ተወሰዱ። ሽንፋ የነሱም ሐገር ቢሆንም ከኖሩበት ቀያቸዉ በትንሽ ባለስልጣናት ትእዛዝ እንደባይተወር ተቆጥረዉ ትግሬ በመሆናቸዉ ብቻ ተፈናቀሉ።

ከዚህን ጊዜ ጀምሮ የቅማንት ህዝብ ጥንካሬ የበረከት እጂ አለበት ማለት ቅማንት ቅማንተኛ ከተናገረ ቅማንት ከዚህ በፊት ቅማንተኛ ከምን ችሎ የበረከት እጂ አለበት አለቀ ሁሉ ነገር ከበረከት ጋር ተገናኘ።  በጣም የሚያስገርመዉ ነገር በረከት ለቅማንት ኮሚቴ በቁጥር ከወገራ እስከ ቋራ ከአንድ ሺ  በላይ ለሚበልጠዉ ለእያንዳንዱ ኮሚቴ ስልሳ ሚሊዮን ብር ሰጥቷል ብለዉ አሁን ደግሞ  አንድ የቅማንት ወጣት ክላሽን ይዞ ካዩ ደብረፂዮን አስታጠቃቸዉ በማለት ህብረተሰቡን ማደናገር ሲሞክሩ፥ በቤተ አማራና ጎንደር ህብረት የሚደገፈዉ መራሹ የአማራ ክልል ልዩ ሀይል በግልጽ በክልሉ ሚዲያ በማዎጅ የቅማንትን ኮሚቴ እጅ እንቆርጣለን ማለቱ ሳይበቃ ለሰሜንና ሰሜን ምእራብ ጎንደር ለተፈጠረዉ የሰዉ የህብትና ንብረት ዉድመት ተጠያቂ መሆናቸዉን ሲያዉቁ ጽንፋቸዉ  መስመር ወጥቶ በክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት የፈጸሙት አሰቃቂ ወንጀል አፋኝነታቸዉ በህዝቡ ላይ ከዚህም ምን ያህል የከፋ እንደነበር ያስረዳል።

ይቀጥላል »»»»> ጭልጋ»»»»> መተማ ዮሀንስ»»»»> ሽንፋ»»»> የቅማንት ህዝብ የሪፈረንደም ዉሳኔ»»»» የ72 እና 69 ቀበሌዎች ሚስጥር»»»» የተፈናቃዮች እርዳታ ፍትሀዊነት መጓደል»»»»» የቀጥላል።

  

 

Leave a Reply