መጋቢት 18, 2012
በሰሜን አሜሪካ ከሚገኙ የጎንደር ተቆርቋሪዎች የተሰጠ መግለጫ
አካፋን አካፋ፤ቶፋን ቶፋ እንበልና ጎንደርን እናድን፥
የአንድን አገር፣ ከተማ፣ ወይም መንደር ሁለንታዊ ህልውና ከህግ ውጭ ማሰብ ከቶ አይቻልም። አገር ማለት እራሱ በውስጡ የሚኖሩት ዜጎች ዕርስ በርሳቻው ተሳስረው የሚኖሩበት ህጋዊ (ህገ-መንግስታዊ) ሥርዓት ከመሆን ውጭትርጉም አይኖረውም። ሰው የማይኖርበት ከሆነ በርሃ፣ ጫካ፣ ምድረበዳ እየተባለ ይጠራል እንጅ አገር አይባልም። በሌላ በኩልሥርዓተ-ህግ ከሌለ ወይም ካልተከበረ ሰው በበርሃ፣ በጫካና በምድረበዳ ውስጥ ከሚኖሩ አራዊት ሊከፋ ይችላል። ግድያ፣ዘረፋ፣ አፈና፣ ቃጠሎ፣ አስገድዶ መድፈር፣ ታጥቆ ማሸበር፣ ማፈናቀል እገታና ቅሚያ ተስፋፍተው ሕገ-አራዊትይነግስበታል። ልክ ፋኖ የሚያተራምሳትን ጎንደር ይመስላል ማለት ነው። ይህን ዓይነት ሁኔታ አርስቶትል የሚባለውጥንታዊውና ታዋቂው የግሪክ ፈላስፋ ከሁለት ሺህ ዓመታት በፊት እንዲህ በማለት ነበር የገለጸው “At his best, man is the noblest of all animals; separated from law and justice, he is the worst” በግርድፉ ሲተረጎም ‘’በላቀ ጎኑ ሰውከእንስሳት ሁሉ ክቡር ነው፤ ከህግና ከፍትህ ሲለይ ግን ከእንስሳት ሁሉ የባሰ ይሆናል’’። በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሰላምትጠፋለች። በጠፋ ሰላም ውስጥ ደግሞ የኢኮኖሚ ዕድገት አይታሰብም። ይልቁንም የለማው ይወድማል። ጥንታውያኑእንዲህ ባለ ችግር ውስጥ በመግባታቸው ይመስላል ህግ የሚባለውን የማህበራዊ ኑሮ መሳሪያ የፈጠሩት። በመስኩምሁራን ዘንድም ህግ የሰው ዘር ወይም ማህበረሰብ ዕራሱን በራሱ እንዳያጠፋ ለመከልከል የዘዬደው ታላቅ የፈጠራውጤት ተደርጎ ይታሰባል። ህግ በባህሪው ዕድገትን እየተከተለ መሻሻልን ወይም መለወጥን፣ ለዜጎች ግልጽ መሆንንናበእኩልነት መተግበርን እንደሚጨምር ይገልጻሉ። ሆኖም ህግ ብቻውን ግን በቂ አልነበረም አይሆንምም። መንግሥትየሚባል ህግን የሚያስተዳድር አካልም መፈጠር ነበረበት። ይህ መንግሥት የሚባል አካል የዜጎቹን ደህንነት ለመጠበቅህግን ያለአድሎና ያለድርድር በቆራጥነት ማስከበር ይጠበቅበታል። ማስተዋል እንደሚቻለው ግን ብዙውን ጊዜ የህግየበላይነትን በተገቢው መንገድ ማስጠበቅ የተሳነውን ወይም ያልፈለገውን መንግሥትና ባለስልጣን ህግ እራሱይበቀለዋል። የበቀሉም ዓይነት መፈንቅለ መንግሥት ወይም የባለስልጣናት ግድያ ሊሆን ይችላል። ዛሬ ኢትዮፕጵያውስጥ ‘’ኢመደበኛ ድርጅቶች’’ የሚባሉት አሼባሪ ቡድኖች እያደረጉ ያሉት ይህንን ነው። መንግሥት የህግ የበላይነትንየማስጠብቅ ተነሳሺነቱንና አቅሙንም ጭምር ለነዚህ ቡድኖች አሳልፎ የሰጠ ወይም በእነሱ የተነጠቀ ይመስላል። ይህንሃቅ በሆደ ሰፊነትና በታጋሺህነት ስም መሸፋፈን አይቻልም። ምክንያቱም የተፈጸሙት ዘር ተኮር ግድያ፣ ቃጠሎ፣ ዘረፋ፣ማፈናቀል፣ እገታና የመሳሰሉት ከባድና ደረቅ ወንጀሎች እንጅ ከመታገስና ከሆደሰፊነት ጋር ግንኙነት የላቸውም።
ከዚህ መንደርደርያ ተነስተን ወደ ጥንታዊቷ፣ ታሪካዊቷና የጎብኚዎች መናሃሪያ ወደሆነችው የጎንደር ከተማና አካባቢዋ በማለፍ ምን ሲደረግ እንደባጀ፣ እንደከረመና አሁንስ ምን እየተደረገ እንደሆነ ባጭሩ እንመልከት። በተለይባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ የጎንደር ከተማ መንግሥት አልባ ነበርች ማለት ይቻላል። ከላይ በመግቢያው የተጠቀሱትከባድና ደረቅ ወንጀሎች በሙሉና በተደጋጋሚ ተፈጽመውባታ። ወንጀሉን በሙሉ ልብ የሚከላከል የመንግሥት ኃይልአልነበራትም። በከተማይቱ ውስጥ የነበሩት የፌደራል ፖሊስና መከላከያ አባላት አብዛኛውን ጊዜ ወንጀል ሲፈጸም ቆሞከመታዘብና የወደቀ አስከሬን ከመልቀም አልፈው ወንጀልን ሲከላከሉ አልታዩም። ከጎንደር ከተማ ባለስልጣናት አንስቶእስከ ፌደራል መንግስት ባለስልጣናት ድረስ በእየለቱ የሚፈጸሙ ወንጀሎችንና ወንጀል ፈጻሚዎችን ጥርት አድርገውያውቃሉ። ይልቁንም የአማራ ክልላዊ መንግሥት ይህን በከባድ ወንጀል ውስጥ የተዘፈቀ አሸባሪ ቡድን በባጀትይደግፈው እንደነበር ምንጮች ይናገራሉ። በመሆኑም በጎንደር ከተማ ውስጥ ለተፈጸመው መጠነ ሰፊና ዘግናኝ ወንጀልመንግሥትንም ከተጠያቂነት የሚያወጣው አይደለም። ሌላው ከዚህ ወንጀለኛ ቡድንና ድርጊቱ ጋር የተያያዘው አሳዛኝጉዳይ የሚዲያ ሺፋን አለመኖርና ኖረም ሲባል ሆን ተብሎ የወንጀለኛ ቡድኑን ስምና ዝና ለመገንባት በታቀደ መልኩሲከናወን መስተዋሉ ነው። በዚህ ዙሪያ ሲንቀሳቀሱ የሚታዩ የሚዲያ ተቋማት ዘረኝነት ክፉኛ የተጠናዎታቸው፣ በጥላቻየተመርዙ፣ በሴረኛነት የበለዙና የሃኬት ፕሮፓጋንዳ ዕውቀት የሚመስላቸው ግብዞች ናቸው። ሞያውን የካዱና ያዋረዱ፤የተማሩት ትምህርትና የሚከተሉት ዕምነት ከገቡበት የጨለማ መንገድ ሊታደጋቸው አቅም እንዳጣ በግልጽ እየታየ ነው።
ለመሆኑ ይህ አሼባሪ ቡድን ማን ነው? ከላይ እንደተጠቀሰው ቡድኑ ዕራሱን “ፋኖ” ብሎ የሚጠራውና አንዳንዶችህዝብን ለመደለል እንደሚሞክሩት “የአማራ የጀርባ አጥንት” ሳይሆን የአማራ የጀርባ ውጋት የሆነው ቡድን ነው። ቡድኑበጎንደር ከተማ ውስጥ በተለያዩ ቀበሌዎች የተለያዩ ካምፖች ሲኖሩት የቡድን መሳሪያዎችን ጨምሮ በተላያዩአውቶማቲክ ጠመንጃዎች እስከ አፍንጫው የታጠቀ ነው። “በተለያዩ ጎበዝ አለቃዎች” የተደራጀ ሲሆን ለአፈና፣ለዘረፋና ለግድያ የሚጠቀምባቻው ቲሞች ወይም ስኳዶች እንዳሉትም ከድርጊቱ መረዳት አያዳግትም። ቡድኑ የሚታውቅየፖለቲካ ዓላማ የሌለው ሲሆን የሚያነሳቸው መፈክሮች ግን በአማራ ሰም ከሚንቀሳቀሱ ጽንፈኛ የፖልቲካ ድርጅቶች ጋርይዛመዳሉ። ይህም ከዚህ አሸባሪ ቡድን በስተጀርባ የፖለካ እጆች መኖራቸውን አመልካች ነው። ከላይ በጥቅሉየተጠቀሱት ሚዲያዎችም በእነዚህ ጽንፈኛ የፖለቲካ ድርጅቶች ዙሪያ እንደሚሺከረከሩ ድርጊታቸው በግልጽ ያሳያል።ይህ ዛሬ ‘’ፋኖ’’ በሉኝ እያለ ጎንደርን እያመሰና እየቆላ የሚገኘው አሸባሪ ቡድን የክራሩ ንጉስ ካሳ ተሰማ በግጥምናበቅላጼ ካሽሞነሞነውና ግርማሞገስ ካላበሰው ‘’ፋኖ’’ ጋር ሲወዳደር በአደረጃጀቱ፣ በተግባሩና በሞራል ቁመናው ፍጹምተቃራኒ ነው። የዛሬው “ፋኖ” ተብዬ ግን የነብሰበላዎች፣ የአቃጣዮች፣ የዘራፊዎች፣ የአስገድዶ ደፋሪዎች፣ የቀማኞች፣የስው አራጆች፣ የገዳዮችና የአጋቾች ጥርቅም መሆኑ በቅርብ ከሚያውቁት በርካታ ምንጮች ጭምር ግልጽ እየሆነመጥቷል። ፋኖ የሚለው ቃል በ1966ቱ አብዮት ወቅት በተማሪዎች ይነሳ እንደነበር ይታውቃል። ከዛ ወዲህ ግን ቃሉየተነሳውና መሰማት የጀመርው በቅርቡ ሲሆን እሱም በይዘቱም ሆነ በቅርጹ በካሳና በተማሪዎች ከተነሳው ፋኖ ጋርአጨማዶ ለመስፋት ቢሞከር እንኳን አይሆንም። ይህ የዛሬው ውል የሌለው አሼባሪ ቡድን “ፋኖ” የሚለውን ስም ይዞወደ አርበኛ አባቶቻችን ለመጠጋትም ሲሞክር ይስተዋላል። ከዚህ ላይ ግልጽ መሆን ያለበት የቀደመው ፋኖ ህዝባዊሲሆን የዛሬው ግን በዉንብድና የሚተዳደር አሼባሪ መሆኑን ነው። በሁለቱ መሃል ያለው ልዩነት የአይጥንንና የዝሆንንየሚያክል ነው። በመሆኑም አይጥ ዝሆንን ትመስል ይሆናል፣ ግን ዝሆንን አታክልም፣ ብሎ በማስረግጥ ማለፍ ይቻላል።
የቆዬውን የፋኖ ክብር ላለመስጠት ሲባል ከአሁን በኋላ አሸባሪ ቡድን እያልን በምንጠራው የወንጀለኞችጥርቅም ላይ መንግስት ሰሞኑን ዕርምጃ መዉሰድ መጀመሩ እየተሰማ ነው። ዕርምጃው እጅግ በጣም የዘገየ ቢሆንምዘገይቶም ቢሆን የመጣውን ከመቀበል ውጭ ጎንደር አማራጭ የላትም። ይልቁንም ሰላሟን አጥብቃ ትሻለች። ገቢያዋተርጋግቶ፣ ሱቆቿ ተከፍተውና የድሮ እንቅስቃሴዋ ተመልሶ ማየትን ትናፍቃለች። መንግሥት ዕርምጃ መውሰድ የጀመረውለጎንደር ከተማና ለኗሪዎቿ ግድ ኖሮት ነው ብለን ለማመን ያስቸግራል። ምክንያቱም ከተማይቱ ባሳለፈቻቸው ፈታኝጊዚያትና ሁኔታዎች ውስጥ ሁሉ በቸልተኝነት ሲያልፍ ተገንዝበናል። አሁን መንቀሳቀስ የጀመረው ግን አሼባሪው ቡድንየህልውና ስጋት ስለደቀነበት መሆኑን ብዙዎች ይስማማሉ። ጉዳዩ ባለስልጣናቱ ሰደድ እሳቱ ከቤቴ እስካልደረሰ ጫካውቢቃጠል ግድ የለኝም በሚል አስደማሚ የኃልፊነት ውድቀት ውስጥ መክረማቸውን በግልጽ አመላካች ነው። ያም ሆነይህ በዚህ ህገ-ወጥ አሼባሪ ቡድን ላይ ዕርምጃ መጀመሩ ተገቢ መኖኑን የማይስማሙ ጥቂት የአሸባሪ ቡድኑ ደጋፊዎችብቻ ለመሆናቸው መረጃዎች ያሳያል። ሰላም እንዲሰፍንና በዕድገት ላይ ለማተኮር ከተፈለገ በጠመንጃና በጉልበት ማሰብመቆም አለበት እንላለን። በመጨረሻም መንግሥት የሚከተሉትን ነጥቦች በትኩረት ተከታትሎ እንዲፈጽማቸውበአንክሮ ለማስገንዝብ እንወዳለን።
- ይህ አሸባሪ ቡድን በጎንደር ከተማ ውስጥና በአካባቢዋ የፈጸማቸውን ወንጀሎች በሙሉ በዓይነትና በአኃዝ ዘርዝሮ ለህዝብ ይፋ እንዲያደርግ።
- የዚህን አሼባሪ ቡድን ዘግናኝ ወንጀል ለመሼፈን ሲሉ በፈጠራ ታሪክና በሃሰት መረጃ ላይ የተመሰረተ ዘገባና የዜና ሽፋን በማቅረብ የቆዩ ችግሮች ይበልጥ እንዲዎሳሰቡና አዳዲስ ችግሮች እንዲፈጠሩ በማድረግ ላይ በሚገኙ የሚዲያ ተቋማት ላይ አስፈላጊ ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ።
- በዚህ አሼባሪ ቡድን ጥቃት የህይዎትና የንብረት ጉዳት ለደረሰባቸው በሙሉ መንግሥት ካሳና ድጎማ እንዲያደርግላቸው።
- አሼባሪው ቡድን የዘረፈው ሃብትና ንበረት ተፈላልጎና ተሰባስቦ ለባለቤቶች እንዲመልሰ እንዲደርግ።
- ማንኛውም ችግር በዛፍ ስርና በአዳራሺ ውስጥ በሚደረጉ ውይይቶች በሰላማዊና ህጋዊ በሆነ መንገድ እንዲፈታ ከወሬ ባለፈ ቁርጠኛ ተግባራዊ እንቅስቃሴ እንዲጀመር።
- በመጨረሻም ዕርምጃው “ዞሮዞሮ ወቅን” (ተመልሶ ከዛው) እንዳይሆን እስከመጨረሻው የመዝለቅ ቁርጠኝነት እንዲኖረው በአንክሮ እንጠይቃለን። በህግ ከተቋቋመው መንግሥታዊ የጸጥታ ኃይል ውጭ ሌላ ታጥቆ የሚንቀሳቀስ ኃይል ወይም ቡድን እንዳይኖር እስከማድረግ የሚዘልቅ ሊሆን ይገባል። ይህም በቀበሌ፥ በወረዳ፥ በዞን፣ በክልልና በአገር አቀፍ ደረጃ ቢሆን የሰላሙንና የመረጋጋቱን ሂደት ያፋጥነዋል በለን እናምናልን።
የህግ የበላይነት ለሁሉም ዜጎች በእኩልነት ይረጋገጥ!
ከጎንድር ተቆርቋሪዎች በሰሜን አሜሪካ።
Recent Comments