ዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ ንጉሰ ነገስት ዘ ኢትዩጵያ
- የትውልድ ዘመን 1810 ዓ.ም የትውልድ ቦታ በቅማንቶች ምድር ዳዋ ዳሞት የእናት ስም ወ/ሮ አትጠገብ ወንድወሰን የአባት ስም ኃይሉ ወልደጊውርጊስ ኃይለማርያም በጎንደር አብዩ እግዚ ኪዳነምህረት ተጠመቁ የልጅነት እድገታቸው እናታቸው በከርከር እና በእናታቸው አባት ወገኞች በኮሶጌና ደፈጫ ኪዳነምህረት አካባቢ ነበር በቸንከር ተክለሃይማኖት ገዳም የቤተ ክህነት ትምህርት ተማሩ ወታደራዊ ክህሎት የተማሩት በአባታቸው ወገን ከሆነው ከደጃዝማች ማሩ ቤት ለተወሰነ ጊዜ ሲኖሩ ነበር አፄ ቴዎድሮስ አምስት ቋንቋዎች አቀላጥፈው ይናገራሉ እነሱም ቅማንትኛ ፣አማርኛ ፣ትግርኛ ፣አረብኛ ፣ ግዕዝ ናቸው።
- የመጀምሪያ ሚስታቸው የጭልጋ ሰራባ ወህኒ ተወላጅ የታዋቂው ቅማንት ሽፍታ ልጅ ወ/ሮ ገሰሱ እንግዳወርቅ ይባሉ ነበር ለመጀመሪያ ጊዜ ትዳር መስርተው ጎጆ ወጥተው በግብርና ይተዳዳሩ የነበረው እያሆ ማርያምና ሰርጢያ መካከል ባለቦታ ነበር የመጀመሪያ ልጇቻቸው መሸሻ ካሳና አልጣሽ ካሳ ይባላሉ፤ አልጣሽ በመጀመሪያ የሚኒልክ ሚስት ሁነው ሲኖሩ በመቅደላ ሚኒልክ ጥለዋቸው ወደ ሸዋ ስለጠፊ የትግራዩን ባላባት ደጃዝማች ባሪያው ጳውሎስን አግብተው ሁለት ልጆችን አፍርተዋል የንግስና ዘመን እ.ኤ.አ ከ1855-1868 ዓ.ም የንግስና የዘር ሃርግ በተረት ተረቱ ፍትሃነገስትና ክብረ ነገስት መቁጠር ስለማይችሉና ስለሌላቸው በአክሱም ፅዩን ማርያም ሳይሆን በደረስጌ ማርያም እንዲነግሱ ተደርጓል
- የአፄ ቴዎድሮስ ምርጥ ተወርዋሪ ልዩ ጦር የቅማንት ብርጌድ ይባላል ታዋቂው የጣሊያን የታሪክ ፀሃፊ Counti Rossini እና የእንግሊዝ መንግስት ልዩ መልዕክተኛ Harmuz Rassam ይህንን በሚገባ በኩሪት ጽፈውታል አፄ ቴዎድሮስ ለመጀመሪያ ጊዜ የሸፈቱት ከጀግናው ወገናቸው ፊት አውራሪ ገልሞ ጋር በቅማንቶች ምድር ቤዛሆ የቅማንቶች የተፈጥሮ ምሽግ (Bezaho natural fortification )የአፄ ቴዎድሮስ ጦር የመጀመሪያ የጦር መሪ ባላምባራስ በኃላ ፊት አውራሪ ገልሞ ይባላል
- የአፄ ቴዎድሮስ የመጀመሪያ እስር ቤቶች ከመቅደላ በፊት የቅማንቶች ምድር ሳር አምባና እንጨት አምባ ይባሉ ነበር ። ለምሳሌ በእንጨት አምባ የጎጃሙ ንጉስ የደጃዝማች ጎሹ ልጅ ተማርኮ በአንድ ወቅት ሲታሰር በዚሁ ነበር የታሰረው የአፄ ቴዎድሮስ ታናሽ እህት የቋረኛው ፊት አውራሪ ገብርዩ ሚስት ታንጉት ትባላለች (የታንጉት ሚስጥርን ያነበባችሁ ገብቷችሗል እንድታነቡት እንመክራለን)
- ሁለተኛ ህጋዊ ሚስታቸው የየጁ ኦሮሞ ተወላጅ የራስ አሊ ልጅ የእቴጌ መነንና የዩሃንስ ፫ኛ የልጅ ልጅ እቴጌ ተዋበች ከሶስተኛ ህጋዊ ሚስታቸው ከእቴጌ ጥሩወርቅ ውቤ ደጃዝማች አለማየሁ ወለዱ በመቅደላ የጥብቅ የውጭ ሃገራትና የሃገር ውስጥ እስረኞች ኃላፊ ቅማንቱ ታማኙ ራስ ኃይሉ ይባሉ ነበር
- የአፄ ቴዎድሮስ የግል ጠባቂ ( personal bodyguard) እና የአፄ ቴዎድሮስን መሳሪያዎችና ትጥቆች የሚይዘው እነ Harmuz Rassam የመሰከሩለት ትንታጉ ታማኙ ቅማንት ፊት አውራሪ ( general ) ወልደ ገብረማርያም ወይም በቅጽል ስሙ የሚጠራው ወልደጋብር ነበር ። ይህ ጀግና ታማኛቸው አፄ ቴዎድሮስ ራሳቸውን ሲሰው ከጎናቸው የነበረና ከወገባቸው የማትለያቸውን ባለጥለት ነጠላቸውን ለክብራቸው ማስታወሻ አንስቶ ታማኝ የአፄ ቴዎድሮስ ወታደሮችን ይዞ ወህኒ አምባ ላይ የነበረውን የጢሶ ጎበዜን ጦር ደምስሶ አምባውን በመያዝ የአፄ ቴዎድሮስ ራዕይ ለማስቀጠል ጥረት አድርጎ በመጨረሻ ሁሉም አልሆን ሲለው ወደ አሰብ ቀይ ባህር አካባቢ ሂዶ የጠፋው ታማኝ ባለሟል ቅማንት ነበር ። Harmuz Rassam ስለ ፊት አውራሪ ወልደ ጋብር ታማኝነት ጥሩ አድርጎ ገልጾለታል።
Recent Comments